የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት /UNICEF/ ሕይወት አድን ምግብ በማጣት ለሞት የተቃረቡና በግጭት መሃል የተጠመዱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናት አጣፋዲ እርዳታ ካላገኙ እንደሚሞቱ አስጠነቀቀ።
ዩኒሴፍ ዛሬ ጄኔቫ ውስጥ ባቀረበው ተማፅኖ፣ ለ81 ሚሊዮን ሕዝብ፣ የ3.3 ቢሊዮን ዶላር ርዳታ የጠየቀ መሆኑ ታውቋል።
ከ81 ሚሊዮኑ ተረዲዎች፣ ገሚሱ ሕፃናት ናቸው ብሏል ዩኒሴፍ።
ዩኒሴፍ ከጠየቀው የ3.3 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ 1.4 ሚሊዮን የሚመደበው በሶሪያ ጦርነት ውስጥ በተጠመዱና በስደት አምስት አጎራባች ሀገሮች ውስጥ ለሚኖሩ 17 ሚሊዮን ተጎጂዎች ሲሆን ግማሹ ሕፃናት ናቸው፡፡ ሊሽላይን ዘገባ ልካለች፣ ትዝታ በላቸው ታቀርበዋለች።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።