በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩኒሴፍ በአፍሪካ ህፃናት ጉዳይ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በአፍሪካ ሳህል ቀጠና አካባቢ እየተባባሰ በመሄድ ላይ ያለው ግጭት ዋናዎቹ ሰለባዎች ወደ አምስት ሚልዮን የሚጠጎ ልጆች መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት /UNICEF/ ገልጿል።

የልጆች የሰብአዊ መብት በአስከፊ ሁኔታ እንደሚጣስ /UNICEF/ ሲያስረዳ ይጠለፋሉ፣ ለውትድርና ይመለመላሉ፣ ጾታዊ ጥቃትና ሌሎች ዓይነት በደሎች ይፈጸሙባቸዋል ይላል።

ቡርኪና ፋሶ፣ ማሊና ኒጀር ውስጥ የሚፈራረቅ ድርቅና የጎርፍ መጥለቅለቅም የታከለባቸው በርካታ ችግሮች በልጆችና በቤተሰቦቻቸው ላይ ስቃይ እያደረሱ መሆናቸውን የህፃናት መርጃው ድርጅት ጠቁሟል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG