በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮሌራ በአፍሪካ ሥጋት ፈጥሯል - ዩኒሴፍ


የዩኒሴፍ ቢሮ ጄኔቫ
የዩኒሴፍ ቢሮ ጄኔቫ

ኢትዮጵያን ጨምሮ በአስር የአፍሪካ አገራት በመሰራጨት ላይ ያለው ኮሌራ፣ በከፍተኛ ወረርሽኝ መልክ እንዳይዛመት መስጋቱን የተመድ የሕፃናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) ገልጿል።

በተለይም በዛምቢያ እና ዚምባቡዌ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል።

የድርጅቱ የምሥራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ክልል አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ፖል ግዋኩም እንዳሉት፣ በ10 አገራት ውስጥ በመዛመት ላይ ባለው ውሃ ወለድ በሽታ 200 ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች የተጠቁ ሲሆን፣ 3 ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

ከአስሩ አገራት ውስጥ ኢትዮጵያ፣ ሞዛምቢክ፣ ታንዛኒያ፣ ሶማሊያ፣ ዛምቢያና ዚምባቡዌ ከፍተኛ የኮሌራ ቀውስ ውስጥ እንደሆኑ ዶ/ር ፖል ግዋኩም ተናግረዋል።

የተበከለ ውሃ መጠጠጣት፣ ተገቢ የንጽህና አጠባበቅ አለመኖር፣ ጎርፍ እና ድርቅ የኮሌራ ወረርሽኝን እንደሚያባብሱ አማካሪው ጨምረው ገልጸዋል።

የበሽታው ሥርጭት በወቅቱ በቁጥጥር ሥር ካልዋለ፣ በዛምቢያ እንደሆነው ትምህርት ቤቶችን መዝጋት ሊያስገድድ እንደሚችልና ሕፃናትን ከትምህርት ቤት ውጪ ሊያደርግ እንደሚችል አማካሪው ጨምረው ገልጸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG