የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛው የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ተከከታታይ አካል በዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት የመጨረሻ ጉባኤው፣ ወደ እስራኤል የሚላክ የጦር መሳሪያ እንዲታገድ የሚጠይቀውን እርምጃ እያጤነ ነው።
የተከታታይ ውሳኔዎቹ አካል በሆነው በዚህ መድረክ የቀረበው የውሳኔ ረቂቅ ሀገራት “ለእስራኤል የጦር መሳሪያዎችን እና ሌሎች ወታደራዊ መሳሪያዎችን መሸጥ፣ ማስተላለፍ እና ማዛወር እንዲያቆሙ” የሚጠይቅ ነው።
ባለፈው መስከረም 26 በሃማስ የተመራ የታጣቂዎች ቡድን ወደ ደቡብ እስራኤል ዘልቆ በመግባት ቁጥራቸው 1ሺሕ 200 የሚደርሱ ሲቪሎችን ከገደለ እና ሌሎች 250 ሰዎችን ማገቱን ተከትሎ መቀስቀሱ ይታወቃል። በእስካሁኑም ውጊያ ከ33ሺሕ በላይ ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ቁጥራቸው 75 ሺሕ 600 የሚደርሱ ሌሎች መቁሰላቸውን የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አመልክቷል።
የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ይፋ ያደረገው ይህ አሃዝ፣ ከዚህ ውስጥ ምን ያህሉ ሲቪሎች፤ ምን ያህሉ ደግሞ ተዋጊዎች መሆናቸውን ግን አይለይም። ሆኖም ሴቶች እና ህጻናት ከሟቾች ቁጥር ሁለት ሦስተኛውን እንደሚይዙ አስታውቋል።
መድረክ / ፎረም