(ይህ ገፅ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ኮምፕዩተርዎ ከአንድ በላይ ድምፅ ማጫወቻ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፅሁፍ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸው፡፡)
ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ስደተኞች ሱዳን ውስጥ በተለይ ምሥራቅ ሱዳን ውስጥ ብዙ መከራ እየደረሰባቸው፣ ብዙ ግፍም እየተፈፀመባቸው መሆኑን በተደጋጋሚ ይናገራሉ፡፡
ብሦቶቻቸውን ለብዙ አባላት ቢያሰሙም ከጥቃት አድራሽ በስተቀር የ“አለሁ” ባይ እጅ እንደማይደርስላቸው ነው የሚናገሩት፡፡
በተለይ በሦስቱ የምሥራቅ ሱዳን ሸገራብ መጠለያ ሠፈሮች ውስጥ የሚገኙት ስደተኞች የእርዳታና የድጋፍ አቅርቦት የማያገኙ ከመሆኑ፣ ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነርም ቢሆን ጥበቃና ከለላ ባለማግኘታቸው በተጨማሪ በተለያዩ አጋጣሚዎችና በተከታታይ የውንብድና አድራጎቶች ይፈፀሙባቸዋል፡፡
ዝርዝሩን ያድምጡ።
(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከዚህ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )