በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከመኖሪያው የተፈናቀለ አንድ ሰው ብዙ ነው


የዓለም የስደተኞች ቀን ሰኔ 13 ቀን ታስቦ ዋለ፡፡

ባለፈው የአውሮፓዊያን ዓመት በዓለም ዙሪያ 4.3 ሚሊየን ሰው ከሚኖርበት አካባቢ በኃይል መፈናቀሉን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር አስታወቀ፡፡

ዩኤንኤችሲአር ዛሬ እየታሰበ ያለውን የዓለም የስደተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ባወጣው መልዕክት “ዓለም ለስደተኞች ጉዳይ ከሚያስገኛቸው መፍትሔዎች ይልቅ ተፈናቃዮችን በፈጠነ ሁኔታ እያፈራ ነው” ይላል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ትናንት ባዘጋጀው አንድ ሥነ-ሥርዓት ከኤርትራ እሥራኤል ውስጥ የሚገኙትንና ስደተኞችን የሚረዱትን ሲስተር አዘዘት ሃብተዝጊ ኪዳኔን ሸልሟል፡፡

ከኢትዮጵያ፣ ከኤርትራ ከሱዳንና ከሌሎችም የአፍሪካ ሃገሮች እየተፈናቀሉ ለሥቃይና ለእንግልት የሚዳረጉ ስደተኞች ጉዳይ እንዲሰማ የሚታገሉና አውሮፓ ውስጥ የሚገኙት የአጃንሲያ ሃበሻ መሥራችና መሪ አባ ሙሴ ዘርዓይ ዓለም ለስደተኞች ትኩረት እንዲሰጥና የተሻለ ከለላ ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ እንዲሠራ አሳስበዋል፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከማጫወቻዎቹ አንደኛውን ብቻ አስቀርተው የቀሩትን ያቁሟቸው፡፡)


XS
SM
MD
LG