በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲስ ሪፖርት ስለስደተኞች


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ባለፈው ዓመት ከ9 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች፣ በግጭትና በመዋከብ ተግባር ምክንያት ከመኖሪያቸው እንደተፈናቀሉ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰደተኞች አገልግሎት ያወጣው ዘገባ ገልጿል።

በዓለም ዙሪያ ለመሰደድ የተገደዱት ሰዎች ብዛት፣ 79.5 ሚልዮን መድረሱን ዘገባው ገልጾ፣ ይህን ያክል ብዛት ያለው ተፈናቃይ ሲታይ ለመጀመርያ ጊዜ መሆኑን ጠቁሟል።

የስደተኞቹ አገልግሎት ዘገባ ያወጣው፣ በዓመታዊ ዘገባው ሲሆን፣ በመጪው ቅድሜ ታስቦ ከሚውለው የስደተኞች ቀን፣ ቀድሞ የወጣ መሆኑ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት ከዓለም ህዝብ አንድ ከመቶ በላይ ወይም፣ ከእያንዳንዳቸው 97ሰዎች፣ አንድ ሰው ተፈናቃይ ነው ይላል ዘገባው።

ወደ 80 ሚልዮን ከሚጠጉት ተፈናቃዮች አባዛኞቹ፣ በሀገር ውስጥ ከመኖርያቸው የተፈንቀሉ ሲሆኑ፣ 29.6 ሚልዮን ወደ ሌሎች ሃገሮች ተሰደው ጥግኝነት የጠየቁ መሆናቸውን፣ የስተደተኞች አገልግሎቱ ዘገባ ጠቁሟል።

XS
SM
MD
LG