በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የስደተኞቹ ኮሚሽን የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ ደርሷል


በቅርቡ በትግራይ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞችን ማጥቃት እንዲቆም የጠየቀ የሰላማዊ ሰልፍ በተባበሩት መንግሥታት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሲካሄድ
በቅርቡ በትግራይ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞችን ማጥቃት እንዲቆም የጠየቀ የሰላማዊ ሰልፍ በተባበሩት መንግሥታት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሲካሄድ

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ኤርትራውያኑ ስደተኞች ወደ ሚገኙባቸው በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ወዳሉት ሁለት የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ መግባት መቻሉን ዛሬ ጄኔቭ ላይ በሰጠው ጋዜጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ቦሪስ ቸሽርኮቭ፣ ይሁን እንጂ የአካባቢው ጸጥታ ሁኔታ አሁንም ያልተረጋጋ መሆኑን ገልጸው ስደተኞቹ አሁንም ችግር ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ ድርጅቱ አያይዞም በአማራና አፋር ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት የተፈናቀሉት አዳዲስ የስደኞች ሁኔታም ያሳሰበውም መሆኑን አስታውቋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞቹ ድርጅት UNHCR እና አጋሮቹ ኤርትራውያኑ ስደተኞች ወደ ሚገኙበት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ወዳሉት አኒ እና አዲ ኻሩሽ የመጠለያ ጣቢያዎች ተመልሰው መግባት መቻላቸው ተገልጿል፡፡

የስደተኞቹ ኮሚሽን የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ ደርሷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:20 0:00

እኤአ ከሀምሌ 13 ጀምሮ በአካባቢው የነበረው ግጭት የ UNHCR ሠራተኞችን ወደ መጠለያው ካምፖቹ እንዳይደርሱ አግዷቸው ቆይቷል፡፡

በሁለቱም መጠለያ ካምፖች ውስጥ ለሚገኙት 23 ሺ ሰዎች የሚሰጠው አስቸኳይ እርድታ እኤአ ከነሀሴ አምስት ጀምሮ መሰጠት የተመጀመረ መሆኑም በመግለጫው ተመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ አሁንም ድረስ የደህንነቱ ሁኔታ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች ዘንድ ለመድረስ ያለው ሁኔታ ውስብስብና አስቸጋሪ ነው፡፡ እንደ ጤና እንክብካቤና ንጹህ የመጠጥ ውሃ የመሳሰሉት መሠረታዊ አገልግልቶችም አልቀዋል ሲል ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

የመንግሥታቱ የስደተኞች ድርጅት እና የኢትዮጵያው ከስደተኞች ተመላሽ ድርጅት በጋር በመሆን ከዳባት አቅራቢያ ለስደተኞች አዲስ ወዳቋቁምት አስቸኳይ የመጠለያ ካምፕ ውስጥ የማስገባት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውና የመጀመሪያዎቹን 135 ስደተኞችን ማስገባታቸውን ገልጸዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ውስጥ ወደ ትግራይ ያለው የሰብአዊ ተደራሽነት የተሻሻለ ሲሆን የመንግሥታቱ ድርጅት የእርዳታ ሰራተኞችና አስቸኳያ እርዳታዎችን የጫኑ 12 ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸው ተመልክቷል፡፡

ካለፈው ነሀሴ ወር ጀምሮ የመንግሥታቱን የእርዳታ ድርጅትና የኢትዮጵያ ከስደት ተመላሾች ድርጅት ጋር በመሆን ወደ አዲስ አበባ ለተሰደዱ ለኤርትራውያኑ ስደተኞች ጊዚያዊ የመታወቂያ ካርድ መስጠታቸውም ተገልጿል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት፣ በአማራና አፋር ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት የተፈናቀሉት የአዳዲስ በርካታ ተፈናቃዮች ጉዳይ ያሳሰበው መሆኑም አስታውቋል፡፡

ከአካባቢው ባለሥልጣናትና መንግሥታቱን ድርጅት ጨምሮ ከአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች እስካሁን ወደ 100 ሺ ሰዎች ከአማራ፣ ከአፋር ደግሞ ወደ 70 ሺ ሰዎች የተፈናቀሉ መሆኑን አመልከተዋል፡፡

ተጨማሪ እርዳታ የጠየቀው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት ወደ 101.3 ዶላር ወይም ከተጠየቀው 61 ከመቶ የሚሆነው ወደ 96ሺ የሚሆኑ የኤርትራውያን ስደተኞችን፣በትግራይ 650ሺ የሚደርሱ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን፣ እንዲሁም በምስራቅ ሱዳን የሚገኙ ወደ ወደ 120ሺ የሚደርሱ ኢትዮጵያውን ስደተኞችን ለመርዳት ያስችላል ብሏል፡፡

በመጨረሻም የተባበሩት መንግሥታ የስደተኞች ኮሚሽን፣ ሁሉም የግጭቱ ተሳታፊ ወገኖች፣ በዓለም አቀፍ የሰብ አዊ ህግ መሠረት፣ ግዴታቸውን በመወጣት፣ አስቸኳይ እርዳታ የሚሹ ወገኖች ደህንነት የተጠበቀ እንዲሆንና፣ ሙሉ ተደራሽነት እንዲኖር እንዲያደርጉ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

XS
SM
MD
LG