ኡምኩሉ የሰደተኞች ሰፈር ከምፅዋ ወደብ ወደ 10 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ሲሆን ከሰኔ ወር አንስቶ ከ2,100 በላይ የሚሆኑ የሶማሊ ስደተኞች ተጠልለውበት ነበር። ከነሱም 1,300 የሚሆኑት አሁን ሰሜን ኢትዮጵያ መግባታቸውን የሰደተኞቹ አገልግሎት ዘገባ ጠቅሷል።
ለ20 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ የሶማሊ ስደተኞችን ሲያስተናግድ የቆየውን ሰፈር ሌላ አማራጭ ሳያቀርቡ መዝጋት ከባድ ሥጋት ያስድራል ሲሉ በአፍሪካ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰደተኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ ራኦፍ ማዞ አስገንዝበዋል።
የስደተኞቹ አገልግሎት 1,300 የሚሆኑትን ከኤርትራ ወደ ትግራይ የገቡትን ሶማሊ ስደተኞችን በሀገሪቱ ደቡባዊ ክልል በሚገኘው መልካዲዳ ለማስፈር ከኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ጋር እያስተባበሩ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
ኢትዮጵያ ውስጥ 257,000 የሚሆኑ የሶማሊ ስደተኞች እንዳሉ የስደተኞቹ አገልግሎት ዘገባ ገልጿል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ