በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ኮሚሽነር በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ


የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ

በትግራይ ክልል ያለው ሰብአዊ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን የገለፁት የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ የቴሌኮሙኒኬሽን እና የባንክ አገልግሎት መቋረጥም ሁኔታውን እንዳባባሰው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ችግሩን ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት አደንቃለሁ ያሉት ኮሚሽነሩ የተባበሩት መንግስታት እና ሌሎች የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ ግን የሰዎች ስቃይ እንዳይባባስ ለማድረግ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ከህፃፅ እና ሽመልባ ካምፖች የተበተኑት ከ15- 20 ሽህ የሚሆኑ ኤርትራውያን ስደተኞች ጉዳይም ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።

በትግራይ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ እንደሚባል የጠቀሱት ኮሚሽነሩ እንደሳቸው የጎበኘ ግን ውስብስብ መሆኑን እንደሚረዳ ጠቁመዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የተመድ ኮሚሽነር በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:44 0:00


XS
SM
MD
LG