በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በሱዳን የስደተኞች ቁጥር እየጨመረ ነው፡ የጤና ሁኔታው እያሽቆለቆለ ነው” ተመድ


ፎቶ ፋይል፦ ሰዎች በጭነት መኪና ተሳፍረው ካርቱምን ለቀው ሲወጡ
ፎቶ ፋይል፦ ሰዎች በጭነት መኪና ተሳፍረው ካርቱምን ለቀው ሲወጡ

እየተባባሰ የመጣውን ጦርነት ሸሽተው አገር ጥለው የሚሰደዱት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በሚገኝባት በሱዳን እና በአጎራባቾቿ ሀገራት የጤና ሁኔታ እያሽቆለቆለ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማት አስጠነቀቁ፡፡

ጦርነቱ ከመቀስቀሱ በፊት 4.5 ሚሊዮን ሱዳናውያን ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን ከ 3ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት እዚያው ሱዳን ውስጥ ሌሎች 800,000 ደግሞ ወደ ቻድ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ግብፅ እና ኢትዮጵያ ተሰድደዋል፡፡

ተቃናቃኞቹ ጄኔራሎች ወደ ጦርነት ከገቡ ወዲህ፣ ከአራት ሚሊዮን የሚበልጡ ተጨማሪ ሰዎች መፈናቀላቸውን የ ተ መ ድ የስደተኞች ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

“የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን አባላት በሚገኙበት በሱዳን ያለው ችግር አሁን በእጃችን ባለው ዓቅም ሊሰጥ ከሚችለው ዕርዳታ በእጅጉ የገዘፈ ነው” ሲሉ የ ዩ ኤን ኤች ሲ አር ቃል አቀባይ ዊሊያም ስፒንድለር ተናግረዋል፡፡

ቃል አቀባዩ በኋይት ናይል ክፍለ ግዛት ያለው የመድኃኒት፣ የህሙማን እና ቁስለኞች እንክብካቤ የሰው ኃይል እጥረት መኖሩን አመልክተዋል፡፡

አያይዘውም “ግጭቱ ከጀመረ ወዲህ ከ144,000 በላይ ከካርቱም የተፈናቀሉ አዲስ ስደተኞች የመጡበትን አስሩንም የፍልስተኞች ካምፖች፣ የጤና እና የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎትን በእጅጉ እንዳስተጓጎለው ገልጸዋል፡፡

ብዙ ቤተሰቦች በሚያሳዝን ሁኔታ እጅግ ካለ በቂ ምግብ እና መድሃኒት ለሳምንታት ተጉዘው በጎረቤት ሀገራት ድንበር መግቢያዎችን እና መተላለፊያ ማዕከላት ተዳክመው እየደረሱ ነው” ሲሉ ቃል አቀባዩ አክለዋል፡፡

"እኤአ ከግንቦት 15 እስከ ሀምሌ 17 በነበረው ጊዜ ውስጥ ከ300 በላይ የሚሆኑት በተለይም ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት፣ በኩፍኝ እና በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ሞተዋል" ሲሉም ቃል አቀባዩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ጦርነቱ አራተኛ ወሩን የያዘ ሲሆን የዐለም የጤና ድርጅት በጸጥታው መደፍረስ እንዲሁም ባለው የመድሃኒት፡ የህክምና ቁሳቁስ፡ የኤሌክትሪክ አና የውሃ ዕጥረት የተነሳ የጤና አገልግሎት ማቅረብን እጅግ አንዳደረገው አመልክቷል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት የምግብ እና ግብርና ተቋም (ፋኦ) በበኩሉ የሱዳን የምግብ ቀውስ እየተባባሰ መሆኑን አስታውቆ በአሁኑ ወቅት 20 ነጥብ 3 ሚሊዮን ህዝብ እጅግ ለከበደ ረሃብ መጋለጡን ገልጿል፡፡ አሃዙ አምና ከነበረው ዕጥፍ ያህል መሆኑን ጠቅሷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG