በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ79ኛው የመንግሥታቱ ድርጅት ጉባኤ ሦስተኛ ቀን ውሎ


የ79ኛው የመንግሥታቱ ድርጅት ጉባኤ ሦስተኛ ቀን ውሎ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:11 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የ79ኛው የመንግሥታቱ ድርጅት ጉባኤ ሦስተኛ ቀን ውሎ

የመንግሥታቱ ድርጅት ሦስተኛው ቀን ጉባኤ ሱዳን፣ ኬኒያ፣ ማላዊ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሌሴቶ እና በርካታ የአፍሪካ መሪዎች የየሀገራቶቻቸውን ትኩረት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በተለይም የኬንያው ፕሬዚደንት ዊልያም ሩቶ ተ.መ.ድ የጸጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ኅብረትን የጸጥታ ቢሮ በገንዘብ መደገፍ አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ጄነራል አብዱልፈታ አል ቡርሃን ሀገራቸው በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳለች ገልጸው ይህ ሊሆን የቻለው፤ እርሳቸው አማጺ ሲሉ የገለጹት በጀኔራል ሀምዳን ዳጋሎ የሚመራው የፈጥኖ ደራሽ ወታደራዊ ቡድን፤ ከቀጠናው እና ከዓለም መሪዎች ግጭቱን መቀጠል የሚያስችለው ድጋፍ እያገኘ በመሆኑ ነው ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

በተመሳሳይ የመን እና ሌሎች ሀገራትም ንግግር ያደረጉ ሲሆን የፍልስጤም ዌስት ባንኩ መሪ መሃሙድ አባስ “እስራኤል የዘር ማጥፋት ዘመቻ ነው የከፈተችው የመንግሥታቱ ድርጅት የህጻናት እና ሴቶች እንዲሁም የሲቪሎችን ሞት ለማስቆም በአፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አለበት’ ሲሉ ተማጽነዋል። መሃሙድ አክለውም የእስራኤል የመስፋፋት ዘመቻ ከጋዛ አልፎ ወደ ዌስት ባንክ ዘልቋል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት ከመሪዎቹ ንግግር ጎን ለጎን ጸረ ባክቴሪያ መድሃኒቶችን መላመድ በዓለም ጤና ላይ እንዲሁም ደግሞ ዘላቂ ልማት ግቦችን በማሳካት ላይ የጋረጠውን አደጋ መንግሥታት ተማክረውበታል። የመንግሥታቱ ድርጅትም ሀገራት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩበት በአጀንዳው አካቶታል። በተመሳሳይም የጸረ ኒው ክሌር ጦር መሣሪያዎች ላይ ግንዛቤ እና ቃል ኪዳን ማደስ ጎን ለጎን ትኩረት ተሰጥቶበት ውይይት ተደርጎበታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG