በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ታሪክ የነፃነት ወገን ነች" - ፕሬዚዳንት ኦባማ ለተመድ ያደረጉት ንግግር


ኒው ዮርክ ላይ ሲካሄድ በሰነበተውና 14ዐ የሚሆኑ የመንግሥታትና የሃገሮች መሪዎች በተገኙበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ የሐሙስ ውሎ ላይ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ፕሬዚዳንቶች ተናግረዋል፡፡

ኒው ዮርክ ላይ ሲካሄድ በሰነበተውና 14ዐ የሚሆኑ የመንግሥታትና የሃገሮች መሪዎች በተገኙበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ የሐሙስ ውሎ ላይ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ፕሬዚዳንቶች ተናግረዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የሃገራቸውን ሠላም፣ የውጭ ፖሊሲና ሰብዓዊ መብቶችን ያካተተ ሰፊ አድማስ ያለው ንግግር ነው ያደረጉት፡፡ በዚህ ንግግራቸው ፕሬዚዳንቱ በሴቶች ላይ የሚካሄደው አመፃ እንዲያከትም ዓለም እንዲተባበር አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም ለያዙት የመካከለኛው ምሥራቅ የሠላም ጥረትም መሪዎቹ ድጋፍ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል፡፡ ከሁሉም ዓይነት የአስተዳደር ሥርዓቶች አሸናፊው ዴሞክራሲ መሆኑን ታሪክ እንደሚመሰክርም ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ መድረክ ላይ የተናገሩት የኢራን ፕሬዚዳንት ማኅሙድ አሕመዲነጃድ በመስከረም 1994ቱ ጥቃት ውስጥ የራሷ የዩናይትድ ስቴትስ እጅ አለበት ብለው ብዙ አሜሪካዊያንና ብዙ መንግሥታትም እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

ይህ የኢራኑ መሪ ንግግር በዩናይትድ ስቴትስ፣ በብዙ የአውሮፓና የሌሎችም አካባቢዎች ልዑካን ዘንድ ቁጣን አጭሯል፡፡ ብዙዎቹም ንግግራቸውን እየረገጡ ከአዳራሹ ወጥተዋል፡፡

ዝርዝሩን በ"የመንግሥታቱ ድርጅት ጉባዔ ያድምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG