ኒው ዮርክ —
ከአፍሪካ ጋር በተለያዩ የጋራ ጥቅም ባላቸው ጉዳዮች ላይ አብሮ የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ትናንት ከዘጠኝ የአፍሪካ መሪዎች ጋር የምሳ ላይ ስብሰባ አድርገው አህጉሪቱ ሰፊ ዕድሎች ያሏት መሆኑን የሚገልፅ ንግግር አድርገዋል፣ ተወያይተዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ከ72ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ጎን የተደረገው፣የፀጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ስብሰባ በሰላም ተልዕኮ ማሻሻያዎችንና የግጭቶች ማስወገጃ አጀንዳ ላይ ተነጋግሯል፡፡
ስብሰባውን የመሩት የኢትዮጵያው ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ናቸው፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ከፍተው ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ