በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ድርጅቱ ለአማራና አፋር ተፈናቃዮች አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት እርዳታ ሰጥቻለሁ አለ


ዩኤንኤፍፒኤ
ዩኤንኤፍፒኤ

የተባበሩት መንግሥታት የሥነ ህዝብ ፈንድ ዩኤንኤፍፒኤ ተወካይ በአማራ ክልል ለሚገኙ 700ሺ ተፈናቃዮች የሚያደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በአማራና በአፋር ክልልም በደረሰው ሰብ አዊ ቀውስ ለተጎዱት እስካሁን ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ የጤና መገልገያዎችን ማበርከቱንም አመልክቷል፡፡

ድርጅቱ እኤአ ሰፕቴምበር 22 በአማራ ክልል ኮሞቦልቻ ውስጥ በአካባቢው በደረሰው ሰብአዊ ቀውስ ለተጎዱት ተፈናቃዮች የሚውል የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን፣ የድርጅቱ ተወካይ ሚስ ዴንያ ጌይል፣ ለወቅቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ደረጀ ጉተማ ማስረከባቸውን ጠቅሷል፡፡

ሚስጌይል በርርክቡ ወቅት ባሰሙት ንግግር ዩኤንኤፍፒኤ በዛሬው እለት እዚህ የተገኘው በአማራ ክልል ለተፈናቀሉት 700ሺ ሰዎችና የተጨናነቁት የጤና ተቋማት የህይወት አድን አገልግሎታቸውን እንዲሰጡ የምናደርገው ድጋፍ የሚቀጥል መሆኑን በለማረጋግጥ ነው” ብለዋል፡፡

ዩኤንኤፍፒኤ 22 ለሚደርሱ የጤናተቋማት ከ200ሺ በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃዮች 20ሺ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ፣ ለአስቸኳይ ጊዜ የሚውል ሥነ ተዋልዶ ጤና መገልገያ አበርክቷል፡፡ በአፋር ክልልም እንዲሁ በሰብአዊ ቀውሱ ለተጎዱት በተመሳሳይ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ፣ ለአስቸኳይ ጊዜ የሚውል ሥነ ተዋልዶ ጤና መገልገያዎች የተበረከቱ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

በትግራይ የተከሰተው ግጭት በመዛመቱ፣ በአማራና በአፋር ግጭቱ ከተከሰተበት እኤአ ከሀምሌ 2021 ጀምሮ ወደ 900ሺ የሚደርሱ አዲስ ተፈናቃዮች መኖራቸውን ድርጅቱ አመልክቷል፡፡ የአከባቢ አየር ለውጡና በማህበረሰቦቹ መካከል የተፈጠረው ግጭት አፋርና አማራ ክልልን ጨምሮ ወደ 5ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን እየጎዳ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ድርጅቱ አስቸኳይ እና የህይወት አድን የጤና እርዳታ የሚሹ በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃይ ሴቶችና ድርስ ልጃገረዶች ህይወት በተለየ ሁኔታ የሚያሳስበው መሆኑን አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG