ዋሺንግተን ዲሲ —
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ፣ በያዝነው ሰኔ ወር 4.8 ሚሊዮን የሥራ ዕድል በመከፈቱ፣ የሥራ ጥነት ቁጥር 11.1 ከመቶ ሆኗል። የሥራው ዕድል ለሁለት ወራት በተከታታይ እንደተሻሻለ ተገልጿል።
የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ትናንት የወጣው አዎንታዊ የሥራ እድል ወሬ፣ የአሜሪካ ኢኮኖሚ ኮሮናቫይረስ ካደረሰበት ጉዳት ማገገሙን ያሳያል ብለዋል።
ይህ መልካም ወሬ የተሰማው የሀገሪቱ ምክር ቤት፣ በቫይረሱ መዛመት ምክንያት የደረሰውን ጉዳት ለማቃለል ሲል የመደበው ድጎማ፣ ሊያብቃ በታቃረበበትና ዓለም አቀፉ ወረርሽኝ በአዲስ መልክ በተዛመተበት ወቅት ነው።