በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቱኒዚያ ከሊቢያ በሚያዋስናት ድምበር መካከል መፈናፈኛ ያጡ ስደተኞችን መልሳ ተቀበለች


ፍልሰተኞቹ ዛፍ ሥር ተጠልለው፡፡
ፍልሰተኞቹ ዛፍ ሥር ተጠልለው፡፡

ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት የተሰደዱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች፣ አደገኛ ወደሆነው የሊቢያ ባለቤት አልባ የድንበር ክፍል ተገፍተው፣ ለሳምንት ያለምንም መሰረታዊ አቅርቦት ከቆዩ በኃላ፣ ወደ ቱሪዚያ እየተመለሱ መሆኑን ሰብዓዊ እርዳታ ተቋማት አስታወቁ።

ስደተኞቹ በዚህ ወር መጀመሪያ ወደ ሊቢያ ድንበር እንዲገቡ የተገደዱት፣ ስፋክስ በተሰኘው የቱሪዚያ ወደብ ከተማ ከተፈፀመ ግድያ ጋር በተገናኘ፣ ከፀረ-ስደተኛነት እና ዘረኝነት ጋር የተያያዘ ውጥረት እየጨምረ በመምጣቱ ነው። የወደብ ከተማዋ፣ በሜዲትራኒያን ባህር ላይ አደገኛና አንዳንዴም ገዳይ በሆኑ የጀልባ ጉዞዎች ወደ ጣሊያን የሚያሻግሩ ህገወጥ አዘዋዋሪዎች የሚገኙበት ማዕከል ነው።

ከነዚህ ጀልባዎች መካከል አንዷ እሁድ እለት በቱኒዚያ ባህር ዳርቻ ላይ የሰጠመች ሲሆን፣ የወደብ ጠባቂዎች 11 ሰዎችን ሲያድኑ፣ አንድ አስክሬን ማግኘታቸውን፣ ሌሎች 10 ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አለመታወቁን የሳክስ አቃቤ ህግ ቢሮ አስታውቋል።

ወደ ቱሪዚያ እና ሊቢያ ድንበር አካባቢ የተገፉት በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ዕጣ ፈንታ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ተቋማት ዘንድ ስጋት በመፍጠሩ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል። በቱሪዚያ የስደት ፖሊሲ ላይም ጥያቄዎች አስነስቷል። ከሳምንታት በፊት፣ ቱኒዚያ የስደተኞች ጀልባዎች ወደ አውሮፓ እንዳያቋርጡ የድንበር አገልግሎቶቿን እንድታጠናክር እና፣ እያሽቆለቆለ ያለውን ኢኮኖሚዋን ለማገዝክ፣ የአውሮፓ ህብረት ለቱኒዚያ ፈላጭ ቆራጭ መንግስት አንድ ቢሊየን ዶላር ሰጥቶ ነበር።

በባለቤት አልባው የድንበር ክፍል ወደ 600 የሚጠጉ አፍሪካውያን ስደተኞች መፈናፈኛ አጥተው መቆየታቸውን ለአሶስዬትድ ፕሬስ የገለፀው ከአይቮሪኮስት የተሰደደ የ29-ዓመት ወጣት፣ ይኖሩበት ከነበረው ስፋክስ ከተማ ዩንፎርም ያለበሱ ሰዎች በውድቅት ለሊት መጥተው ወደ ድንበሩ እንደወሰዷቸው ገልጿል።

ሰብዓዊ ተቋማት ባደረጉት ግፊት፣ የቱኒዚያ ፕሬዝዳንት ካይስ ሰኢድ ስደተኞቹ እንዲመለሱ ትዕዛዝ ከሰጡ በኃላ፣ እሱ እና ወደ መቶ የሚጠጉ ሌሎች ስደተኞች በቱሪዚያ ወደምትገኘው ሜደኒን የተሰኘች ደሴት መዛወራቸውንም አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG