በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"እስላማዊ መንግሥት ነኝ" የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገለፀ


ሶማልያ ያለው “እስላማዊ መንግሥት ነኝ” የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገልጿል። ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ምልመላ የማካሄድ ዓላማ እንዳለው ያመለክታል ተብሏል።

ይህ ማስታወቅያ ባለፈው ወር በሦስት ደቂቃ ቪድዮ መልክ የተለቀቀው በፅንፈኛው ቡድን ደጋፊ ድረ-ገፆች ላይ ሲሆን ኦፊሴላዊው እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ሚድያ ደግፎታል። ቪድዮው የአማርኛ ቃላትን ተጠቅሟል፣ ተጨማሪ ጽሑፎችን በአማርኛ እንደሚያወጣም ተናግሯል ተብሏል።

ማት በረየደን የተባሉ ኬንያ ባለው የሳሃን ጥናትና ምርምር ተቋም የሚሰሩ ተንታኝ እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ያለመረጋጋት ሁኔታን ተጠቅሞ ሙስሊም ማኅበረሰብን የመስበክ ዓላማ አለው ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።

አያይዘውም ተንታኙ ጽንፈኛው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ዕድል እንዳለው ይታየዋል የሚል አመለካከት እንዳላቸው ጠቁመዋል። እስካሁን ባለው ጊዜ በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች ብዙም ባይሳካለትም አፍሪካ ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘትና እንቅስቃሴውን ለማስፋት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ይላሉ ብራይደን።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG