በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩኔስኮ ዓለም የህጻናትን የትምህርት ግብ በማሳካት ወድቋል አለ


ፎቶ ፋይል - የኔፓል ህፃናት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለወራት የተዘጋው ምህርት ቤት ከተከፈተ በኋላ ክፍሎቻቸው እስኪጀመሩ ድረስ እየተጠባበቁ።
ፎቶ ፋይል - የኔፓል ህፃናት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለወራት የተዘጋው ምህርት ቤት ከተከፈተ በኋላ ክፍሎቻቸው እስኪጀመሩ ድረስ እየተጠባበቁ።

የተባበሩት መንግሥታት ዛሬ ሰኞ ባወጣው ሪፖርት ዓለም እኤአ በ2030 ህጻናት አሳታፊ ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት፣ እንዲሁም ለዘለቄታው የሚረዳቸው የትምህርት እድል እንዲያገኙ ለማስቻል ያለመውን ግብ ማሳካት እንዳቃተው አስታወቀ፡፡

የግቡ ተሳታፊ በሆኑ አገሮች ህጻናት ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ ትምህርት እድል እንዲያገኙ፣ ትምህርታቸውን ሳያጠናቅቁ አቋርጠው እንዳይወጡ፣ የጾታ ልዩነት የሚያጠቡ፣ የንባብና የሂሳብ ትምህር ችሎታቸውን እንዲያሻሽሉ፣ የሰለጠኑ መምህራንን ማፍራት፣ የህዝብ ትምህርት ቤቶች፣ ማስፋፋት የመሳሰሉት እንደ አመላካች ግብ የተቀመጡ እንደነበሩ ተመልክቷል፡፡ ይሁን እንጂ የተባበሩት መንግሥታት የትምህር የሳይንስና የባህል ማዕከል ዩኔስኮ አገሮቹ ከወዲሁ እነዚህን ማሳካት አቅቷቸው ወድቀው ታይተዋል ሲል አስታውቋል፡፡

“ይህ ውድቀት ለዓለም መሪዎች ትልቅ የማንቂያ ደወል ሊሆን ይገባል” ያለው ዩኔስኮ ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናት የትምህርት ጥራትና እድል እያጡ መምጣታቸውን አሳስቧል፡፡

የትምህርት ግብ እኤአ በ2015 ከወጡ 17 የዘላቂ ልማት ግቦች አራተኛው ግብ ተደርጎ በተባበሩት መንግሥታት የተወሰደ ቢሆንም፣ እኤአ በ2030 ይደረስበታል የተባለው ጠቅላላ ግብ፣ ከወዲሁ ከሽፎ መታየቱን ዩኔስኮ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG