በሶማሊያ፣ በኢትዮጵያ እና ኬንያ ሰብዓዊ ቀውስ ለመከላከል ከድርጅቱ የአጣዳፊ ጉዳይ ወጭ አርባ አምስት ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚለቅቁ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ እኤአ በ2011 ሶማሊያ ውስጥ እንደደረሰው ያለ ቸነፈር ዘንድሮ እንዳይከሰት ለመከላከል ተጨማሪ ሰባት መቶ ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ኃላፊው ማርክ ሎውኮክ አስታውቀዋል። በሶማሊያው ረሃብ ሩብ ሚሊዮን ህዝብ መሞቱ አይዘነጋም ።
ከተመድ የአስቸኳይ ወጪ ከተመደበው አርባ አምስት ሚሊዮን ዶላር ውስጥ ሰላሳ ሚሊዮኑ ለሶማሊያ፣ አስር ሚሊዮኑ ለኢትዮጵያ ሲሆን አምስት ሚሊዮኑ ደግሞ ለኬንያ የተመደበ መሆኑ ተገልጿል፡፡
“በተለይ የሚያሳስበኝ የሶማሊያ ጉዳይ ነው። በዓመቱ መጨረሻ ወደአምስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ህዝቡዋ የከበደ የምግብ ችግር ላይ ይወድቃል ብለን እናስባለን። ከዚያ ውስጥ የሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮኑ ይዞታ አጣዳፊ ደረጃ ላይ ይደርሳል ሲሉ የመንግሥታቱ ድርጅት ባለሥልጣን አስገንዝቧል።
ዓለም በሶማሊያ ሌላ ረሃብ በዝምታ ማየት የሚፈልግ አይመስለኝም ሲሉ አያይዘውም ከሁለት ዓመታት በፊት ሶማሊያ ላይ የቸነፈር ሁኔታ ሲያንዣብብ ፈጠን ያለ ዕርምጃ በመውሰዳችን ልንከላከለው ችለናል ። አሁንም ተመሳሳይ ዕርምጃ መውሰድ አለብን ነው ያሉት ማርክ ሎውኮክ በግልጽ መናገር የምፈልገው ዕርምጃ ካልወሰድን ብዙ ህይወት እንደሚጠፋ ነው “ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ