በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ የሶማሊያው ረሀብ ከመጨረሻው ጫፍ መድረሱን አስጠነቀቀ


ፎቶ ፋይል፦ በድርቁ ሳቢያ የሞቱ ከብቶች፤ ሶማሊያ እአአ 5/26/2022
ፎቶ ፋይል፦ በድርቁ ሳቢያ የሞቱ ከብቶች፤ ሶማሊያ እአአ 5/26/2022

“ከፍተኛውና አስከፊው ድርቅ በሶማሊያ በራፍ ላይ መሆኑን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እየደረሰን ነው” ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ (ኦቻ) ኃላፊ ማርቲን ግፍሪትስ ዛሬ ሰኞ ሞቃድሾ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስጠነቀቁ፡፡

ግሪፍትስ በመግለጫቸው በድርቅ የተጎዳችው ሶማሊያ ከአስር ዓመት ትንሽ እልፍ ባለ ጊዜ ውስጥ፣ ለሁለተኛ ጊዜ በከፍተኛ የረሀብ አደጋ አፋፍ ውስጥ ትገኛለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ዛሬ ሰኞ ይለቀቃል የተባለው የምግብና የተመጣጠነ ምግብ ሪፖርት ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ባለው ጊዜ ውስጥ፣ በማዕከላዊ ሶማልያ በባይዶዎና በርሃካባ ለሚከሰት ረሀብ ተጫባጭ አመላካቾች መሆናቸውን ግሪፍትስ ተናግረዋል፡፡

አገሪቱን ለመጎብኘት ባላፈው ሀሙስ ሶማሊያ የገቡት የኦቻ ኃላፊ ግሪፍትስ “ባላፉት አጭር ቀናት ውስጥ በርካታ ሶማሊያውያን የተሸከሙትን የስቃይ መጠን መመልከቴ ፍጹም ከልቤ አስደንግጦኛል” ብለዋል፡፡

“በተደጋጋሚ ሳይመጣ የቀረው የዝናብ ወቅት፣ ለአስርት ዓመታት የቆየው ግጭት፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መፈናቀልና፣ እጅግ የተጎዳው ኢኮኖሚ በርካታ ሰዎችን ወደ ከፋው የረሀብ ጫፍ እየገፋቸው ነው”ብለዋል ኃላፊው፡፡

“አሁን ህይወትን ለማዳን በመጨረሻው 11ኛው ሰዓት ላይ እንገኛለን” በማለትም አክለዋል፡፡

የሰብአዊ ድርጅቶች ለበካታ ወራት ማስጠንቀቂያውን ሲያሰሙ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

አሁን በሶማሊያ ያለው የረሀብ ሁኔታ እአአ በ2011 ከነበረውና 260ሺ ሰዎች ከተጠቁበት፣ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከ6 ዓመት በታች ህጻናት ከሆኑበት ረሀብ እጅግ የከፋ መሆኑን በመግለጽ ኃላፊው አስጠንቅቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG