በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ በሠራተኞቹ እሥር መግለጫ ሠጠ


ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ
ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ

ሰሞኑን በኢትዮጵያ የሚገኙ ሠራተኞቹ የታሰሩበት መሆኑን ሲያስታውቀው የነበረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዛሬ ባወጣው መግለጫ 34 የሚሆኑን መፈታታቸውን አስታውቋል፡፡

“ይህ መልካም ዜና ነው ያሉት” የድርጅቱ ቃል አቀባይ ፋራሃን ሳድቅ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ድርጅቱ 36 የሚሆኑን አሁንም በ እስር ላይ መሆናቸውን ገልጸው ባለፈው ዓርብ መታሰራቸውን ይፋ ያደረጉት 10 ሠራተኞቹ አሁንም ያልተለቀቁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በአፋር ሰመራ በኩል ወደ ትግራይ ስለተላኩት የድርጅቱ የጭነት ተሽከርካሪዎችም ሁኔታ የተጠየቁት ቃል አቀባዩ

"አገልግሎታቸውን እንዲገቱ ተደርገው የነበሩት የጭነት ተሽከርካሪዎች ስለ መንቀሳቀሳቸው አላውቅም፡፡ አሽከካሪዎቹ መለቀቃቸው ግን መልካም ዜና ነው፡፡" ብለዋል፡፡

አያይዘውም "ሌሎች ተጨማሪ እርምጃዎችንም ደግሞ ማየት እንፈልጋለን፡፡ ሁሉም ሾፌሮች ሁሉም ሠራተኞቻችን እንዲለቀቁ እንፈልጋለን፡፡ ወደ ትግራይ እንዲደርሱ የተላኩ ተሽከርካሪዎችም ወደ ተላኩበት ቦታ መድረሳቸውን ማረጋገጥ እንፈልጋሉ፡፡ በቅርብ ቀናት እርዳታዎቻችን እንደልብ ማንቀሳቀስ የምንችልበት ትላልቅ ስምምነቶችን መፈራረማችንን ሰምተናል ያ በተግባር ተተርጎሞ ግን ማየት እንሻለን፡፡” በማለት ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG