በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት መንግሥታት ስር ስለሰደደው ዘረኝነት


“ዘረኝነት ይገድላል” የሚል መፈክር ያነገቡ “የጥቁሮች ህይወት ዋጋ አለው” ለሚለው ተቃውሞ በጀርመን በርሊን እኤአ ጁላይ 2/ 2021
“ዘረኝነት ይገድላል” የሚል መፈክር ያነገቡ “የጥቁሮች ህይወት ዋጋ አለው” ለሚለው ተቃውሞ በጀርመን በርሊን እኤአ ጁላይ 2/ 2021

የተባበሩት መንግሥታት የሰአብአዊ መብት ድርጅት ኮሚሽነር ሚሸል ባሽሌት በአፍሪካውያን እና የአፍሪካ ዝርያ ባላቸው ሰዎች ላይ የሚደረገው ሥር የሰደደ ስልታዊውን ዘረኝነትና ጥቃትን በሚመለከት ተጨባጭ እምርጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የድርጅቱ ከፍተኛ ኮሚሽነር እነዚህን ችግሮች ሊያስወግዱ ይችላሉ በሚል ሊወሰዱ ይገባቸዋል ያልዋቸውን ተከታታይ የውሳኔ ሀሳቦችን በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ ሪፖርት ላይ አካተዋል፡፡

ሪፖርቱ እንዲቀርብ የተደረገው ባለፈው ዓመት በዩናይትድ ስቴትስ ሚኒሶታ ውስጥ በአፍሪካ አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ነው፡፡ ከፍተኛ ኮሚሽነሯ “የፍሎይድ ግድያ አብይና ቁልፍ ክስተት ነው” ብለውታል፡፡ ምክንያቱም የዓለምን ትኩረት በአፍሪካውያንና የአፍሪካ ዝርያ ባላቸው ሰዎች ላይ ዘወትር ወደ ሚፈጸመው የሰብ አዊ መብት ጥቃት እንዲዞር አድርጓል፡፡

ሪፖርቱ አፍሪካዊ ዝርያ ባላቸው ወገኖች ላይ የሚደረገውን አድላዊነት አግላይነትና ተመሳሳይ እድሎችን አለማግኘትን፣ እንዲሁም ኢፍትሃዊ በሆነ ሥርዓት ፣በድህነት ተይዘው አቅም አልባ የተደረጉትን ሰለባዎች በሚመለከት ያለውን አጠቃላይ ገጽታ ያሳያል፡፡

ሪፖርቱ በህግ አሰካባሪዎች እጅ የተፈጸሙ አደገኛ ክስተቶች ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ኮሚሽነሯ እንዳሉት ጽ/ቤታቸው ቢያንስ 190 በሚደርሱ አፍሪካውያንና አፍሪካዊ ዝርያ ባላቸው ሰዎች ላይ ስለተፈጸሙ ግድያዎች ሪፖርት እንደደረሳቸው ተናግረዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 98 ከመቶ የሚሆኑት የተፈጸሙት በአውሮፓ ላቲን አሜሪካ እና ሰሜን አሜሪካ ውስጥ ነው፡፡

በእነዚህ ሁሉ ጉዳዮች ውስጥ ፍትህ ቋሚ በሆነ መንግድ ሲጣስ መመልከቱ አስደናቂ መሆኑን ኮሚሽነሯ ተናግረዋል፡፡ ከእነዚህም አንዳንዶቹን ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል

“ከፖሊስ ጋር በተያያዙ አደጋዎች ጎልተው የሚታዩ ሶስት ቁልፍ ችግሮች ቢኖሩ፣ ጥቃቅን መተላለፎች፣ እንደትራፊክ መብራት ጥሰቶች ወይም የድንገተኛ ፍተሻዎች ጊዜ የሚፈጸሙ፣ በተጠሩበት ስፍራ ምላሽ ለመስጠት ፈጥነው የሚደርሱ ህግ አስከባሪዎች በአዕምሮ ህሙማንና የጤና ቀውስ ባላቸው ላይ የሚያደርሱት ችግር፣ ወይም በአደንዛዥ እጽ ላይ የሚካሄድ ጦርነት በሚል የቡድን ወንጀለኞችን ለመያዝ በሚደረጉ የልዩ የፖሊስ ኃይሎች ስምሪት ወቅት የሚፈጸም፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ህግ አስከባሪ መኮንኖች የአፍሪካ ዝርያ ባላቸው ሰዎች ላይ የሚያደርሷቸው የሰብአዊ መብት ጥሰትና በሚፈጽሟቸው ወንጀሎች ተጠያቂ የሚሆኑበት ጊዜ እጅግ አነስተኛ መሆኑ ተዘውትረው የሚታዩ ናቸው፡፡”

የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ፍጹም የተለየ ነው፡፡ ፖሊስ መኮንኑ ደሪክ ሻቪን፣ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ጆርጅ ፍሎይድን ሲገድል፣ በቪዲዮ የታየ ሲሆን፣ ሚሊዮኖች ተመልክተውታል፡፡ እሱም ጥፋተኛ ተብሎ ከ20 ዓመት በላይ ተፈርዶበት ወህኒ ወርዷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ስር ስለሰደደው ዘረኝነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:35 0:00

የጆርጅ ፍሎይድ ወንድም ፊሎኒየስ በቪዲዮ በተላለፈ መልዕክቱ አሁን ድረስ የወንድሙን አሰቃቂ ህልፈት መመልከት የሚረብሸው መሆኑን ተናግሯል፡፡

“በጠራራ ጸሀይ ስቃይ ደርሶበታል፡፡ ይህ በዚህ ዘመን የታየ ዘመናዊ ግድያ ነው፡፡ ምንም መሳሪያ ባትይዝ እንኳ ከፖሊስ ሸሽተህ ለማምለጥ ብትሞክር ከጀርባህ ተኩሰው እንደሚመቱህ ማወቁ ራሱ አስቸጋሪ ነው፡፡ አንተ ምንም መሳሪያ የለህም፣ እነሱ ግን ይህም ሆኖ ነጻ ይወጣሉ፡፡”

እነዚህን ጥልቅና መጠነ ሰፊ ኢፍትሃዊ ጉዳዮች እንዲሁም ከባርነት ቅሪቶች ጋር ተያይዘው ያሉትን ችግሮች ለማስወገድና ፍትህን መልሶ ለማስፈን አጣዳፊ ፍላጎት መኖሩን ኮሚሽነሯ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሯ ካቀረቧቸው ምክረ ሀሳቦች ውስጥ ስር የሰደደ ስልታዊ ዘረኝነት መኖሩን መቀበል ይገኝበታል፡፡ ለሚፈጽሟቸው ወንጀሎች ህግ አሰከባሪዎችም ተጠያቂ የሚሆኑባቸው፣ በጸረ ዘረኝነት ዙሪያ የተቃውሞ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ እንዲኖር፣ በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ መብት እንዲረጋገጥ፣ እንዲሁም ተከታታይና መጠነ ሰፊ የማሻሻያ እምርጃዎች እንዲወሰዱ የሚጠይቁ እርምጃዎችም እንዲወሰዱ በሪፖርቱ ተካተውበታል፡፡

(የቪኦኤ ዘጋቢ ሊዛ ሽላይን ከጀኔቭ ከላከቸው ዘገባ የተወሰደ)

XS
SM
MD
LG