በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር "በሱዳን ብዛት ያለው ሕዝብ በረሃብ የመሞት አደጋ ላይ ነው" ሲሉ አስጠነቀቁ

የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር "በሱዳን ብዛት ያለው ሕዝብ በረሃብ የመሞት አደጋ ላይ ነው" ሲሉ አስጠነቀቁ

ፎቶ ፋይል - ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናት በቦራም ካውንቲ፣ ደቡብ ኮርዶፋን፣ ሱዳን ውስጥ በሚገኝ የተፈናቃዮች ካምፕ ምግብ ለማግኘት እየተጠባበቁ፤ እአአ ሰኔ 22/2024
ፎቶ ፋይል - ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናት በቦራም ካውንቲ፣ ደቡብ ኮርዶፋን፣ ሱዳን ውስጥ በሚገኝ የተፈናቃዮች ካምፕ ምግብ ለማግኘት እየተጠባበቁ፤ እአአ ሰኔ 22/2024

የሱዳን ጦርነት እየተባባሰ ሊሄድ እንደሚችል ያስጠነቀቁት የተመድ የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ከሚሽነር፣ በረሃብ ምክንያት ቁጥሩ የበዛ ሰው ሊሞት እንደሚችል አሳስበዋል።

የከፍተኛ ኮሚሽነሩ ቮልከር ቱርክ ማስጠንቀቂያ የመጣው የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ዳርፉር ጦርነቱ በመባባሱ በተፈናቃዮች መጠለያዎች በረሃብ ለተጎዱ ሰዎች የሚያከፋፍለውን ምግብ ለጊዜው ማቋረጡን ተከትሎ ነው።

“ሱዳን ዘግናኝ ወንጀል የሚፈጸምበትና እና በረሃብ ሰዎች የሚያልቁበት የባሰ ትርምስ አፋፍ ላይ ነች” ሲሉ ከፍተኛ ኮሚሽነሩ በተመድ የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

“ጦርነቱ የመባባሱ አደጋም እንደ አሁኑ ከፍተኛ ኾኖ አያውቅም” ሲሉም አክለዋል።

ከሱዳን መንግሥት ሠራዊት ጋራ በመፋለም ላይ ያለው የፈጥኖ ደራሽ ኅይሉ በተቆጣጠራቸው ሥፍራዎች አስተዳደር ለመመሥረት መንቀሳቀሱ ክፍፍል እና ሁከትን ሊያባብስ እንደሚችል ከፍተኛ ኮሚሽነሩ ጨምረው ገልጸዋል። ከዚህም ሌላ ተዋጊዎቹ ወገኖች የጦር መሣሪያዎች የተራቀቁ መሣሪያዎችም ጭምር አሁንም ከውጭ እያገኙ መሆናቸውን የሰብአዊ መብት ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG