በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካርቱም ውጊያው ቀጥሏል፤ የሰባት ቀናቱ የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሷል


ፎቶ ፋይል፡ የአየር ላይ የቦምብ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ በህንጻዎች ላይ የደረሰው ቃጠሎ፤ ካርቱም፣ ሱዳን
ፎቶ ፋይል፡ የአየር ላይ የቦምብ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ በህንጻዎች ላይ የደረሰው ቃጠሎ፤ ካርቱም፣ ሱዳን

በሱዳን ዋና መዲና ካርቱም ያሉ ነዋሪዎች፣ ዛሬ ረቡዕ፣ በከባድ መሣሪያ የታገዘ ውጊያ እንደነበር ተናግረዋል።

ከትላንት በስቲያ ሰኞ ማታ መጀመር የነበረበት የሰባት ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ወዲያውኑ ተጥሶ፣ በሁለት ተቀናቃኝ ጀነራሎች መካከል የሚደረገው ውጊያ ለአምስተኛ ሳምንት ቀጥሏል።

ባለፈው ቅዳሜ፣ በጀዳ ሳዑዲ አረቢያ በተደረሰው ስምምነት መሠረት፣ ከአደራዳሪዎቹ አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ፣ እንዲሁም ከሁለቱ ተዋጊ ኃይሎች ከእያንዳንዳቸው ሦስት ተወካዮች ያሉት የቁጥጥር ቡድን ተቋቁሞ ነበር።

“ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች እየደወሉ አንዱ የሌላውን ርምጃ እንዳወግዝ በመጠየቅ ላይ ናቸው፤” ብለዋል፣ በሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካይ ቮልከር ፐርዝስ።

የተመድ የጸጥታው ም/ቤት፣ ባለፈው ቅዳሜ የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት በመደገፍ፣ ሱዳን በሲቪሎች ወደሚመራ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር እንድትመለስ ጠይቋል።

በሱዳን፣ ግጭቱ ከመጀመሩም በፊት፣ 15 ሚሊዮን ሰዎች ርዳታ ያስፈልጋቸው እንደነበርና አሁን ቁጥሩ ወደ 18 ሚሊዮን ማደጉን ተመድ አስታውቋል። ችግሩን ለመቋቋም፣ 2ነጥብ6 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ተመድ ባለፈው ሳምንት አመልክቶ ነበር።

XS
SM
MD
LG