በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም ጠባቂ ሀይሎች በአብየ እንዲመደ ቡ ወሰነ


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት እስከ 4200 የሚሆኑ ሰላም ጠባቂዎች በአጨቃጫቂው አብየ ክልል በሰሜንና በደቡብ ሱዳን መካከል ባለው አከባቢ እንዲመደቡ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

15 ቱ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት የኢትዮጵያ ወታደሮች ለስድስት ወራት ያህል ለሰላም ጥበቃ በአብየ እንዲመደቡ ተስማምተዋል። የውሳኔው ሀሳብ የጸደቀው አብየ ከወታደራዊ ሃይሎች ነጻ ቀጠና እንድትሆንና የተባበሩትመንግስታት ድርጅት ውክልና ያላቸው ሰላም ጠባቂዎች እንዲመደቡ ሰሜንና ደቡብ ሱዳን እአአ ሰኔ 20 ቀን ከተስማሙ በኋላ ነው።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሱዳን አምባሳደር Daffa-Alla Elhag Ali Osman “የዚህን ውሳኔ መጽደቅ ሙሉ በሙሉ እናከብራለን። ሌላው ወገንም እንደዚሁ አብየ ከወታደራዊ ሀይል ነጻ እንዲሆን ጥሪ የሚያደርገውን ውሳኔ መጽደቅ ሙሉ በሙሉ እንደሚያከብር በተግባር አሳይቷል።” በማለት አዎንታዊ ምላሽ ሰጥተዋል።

XS
SM
MD
LG