በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አንዲት ከተማን ሲቆጣጠር 300ሺሕ ሰዎች ጥለው ሸሹ


ሱዳናውያን ስደተኞች የህክምና መስጫ ተሰባስበው በኤከር፣ ቻድ፣ እአአ ነሃሴ 15/2023
ሱዳናውያን ስደተኞች የህክምና መስጫ ተሰባስበው በኤከር፣ ቻድ፣ እአአ ነሃሴ 15/2023

በሱዳን በመካሄድ ላይ ካለው ጦርነት ርቀው ደህንነቱ የተጠበቀ ስፍራ ይኖሩ የነበሩ እስከ 300 ሺሕ የሚገመቱ ሰዎች፣ አካባቢያቸው በመጠቃቱ ቤታቸውን ለቀው ለመሸሽ እንደተገደዱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዛሬ አስታውቋል።

ከሱዳን ሠራዊት ጋር በመፋለም ላይ ያለው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ፣ ዋድ ሜዳኒ የተሰኘችውን ከተማ አጥቅቶ ሲቆጣጠር፣ የሱዳን ሠራዊት ለቆ መውጣቱ ተዘግቧል።

የተመድ ዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) እንዳስታወቀው፣ ከ250ሺሕ እስከ 300 ሺሕ የሚገመቱ ሰዎች ጃዚራ የተባለውን አውራጃ ጥለው መሸሻቸውን አስታውቋል።

የሱዳን የዳቦ ቅርጫት እንደሆነች በሚነገርላት ጃዚራ፣ 6 ሚሊዮን ሰዎች እንደሚኖሩባት ይገመታል።

ጃዚራ አብዛኞቹ ከመዲናዋ ካርቱም የመጡ 500ሺሕ የሚሆኑ ተፈናቃዮችን ተቀብላ እንደነበርም ታውቋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በበኩሉ በሥፍራው የሚሰጠውን የምግብ ርዳታ ለጊዜው ማቋረጡን አስታውቋል።

ከካርቱምና ከሌሎችም ሥፍራዎች ጦርነትን ሸሽተው በሥፍራው ይኖሩ የነበሩ 800ሺሕ ተፈናቃዮችን በመመገብ ላይ እንደነበር ፕሮግራሙ አስታውቋል።

እስከ አሁን ዘጠኝ ሺሕ የሚሆን ሕይወት የቀጠፈው ጦርነት፣ ሰባት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችንም አፈናቅሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG