በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ አሁንም ተለዋዋጭ ነው አለ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ አሁንም የማይታወቅና ተለዋዋጭ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ትናንት በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው በትግራይ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ አሁንም እንደተባባሰ መሆኑን ገልጸው፣ በሰመራና አላባ በኩል ብቻ ወደ መቀሌ የሚያደርሰው መንገድ በተፈጠረው ውጥረት ሳቢያ በመዘጋቱ የአቅርቦት ችግር መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡

እኤአ ከታህሳስ 15 ጀምሮ የሰብዓዊ እርዳታን የጫነ አንድም ተሽከርካሪ ወደ ትግራይ አለመድረሱን ተናግረዋል፡፡

እኤአ ከጁላይ 12 ጀምሮ ወደ ትግራይ የገቡ ሰብዓዊ እርዳታን የጫኑ ተሽከርካሪዎች 1ሺ338 ብቻ መሆናቸውንም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡

ይህ እንዲገባ ከሚፈለገው የጭነት ተሽከርካሪ መጠን ጋር ሲተያያ 12 ከመቶ ብቻ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ቃል አቀባዩ የምግብ እርዳታዎችንም ለማጓጓዝ ወደ 60ሺ የሊትር ነዳጅ እንደሚያስፈልግም አስታውቀዋል።

በትግራይ የነዳጅና ጥሬ ገንዘብ በአስቸኳይ የማያደርሳቸው ከሆነ የተባበሩት መንግሥታም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የእርዳታ አቅርቦታ አገልግልቶቻችውን እንደሚያቋርጡ ስቴፋን ዱጃሪች አሳስበዋል፡፡

ቃል አቀባዩ በአፋር አማራና ትግራይ አሁንም የሚፈናቀሉ ሰዎች መኖራቸውን ገልጸው፣ ሁሉ ወገኖች በሦስቱም ክልሎች ዘላቂ የእርዳታ ተደራሽነት እንዲኖር እንዲፈቅዱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG