በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ የአፍሪካ ቀንድ ድርቅ አደጋ አሁንም ብርቱ መሆኑን ተናገሩ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱጃሪች
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱጃሪች

“የኢትዮጵያን የተለያዩ ክፍሎች፣ ኬንያን እና ሶማሊያን ይዞ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ቀንድ ቁጥሩ 22 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ ለከፋ የምግብ ዋስትና ዕጦት ተጋልጧል።” ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱጃሪች በዛሬው መግለጫቸው ተናገሩ።

ቃል አቀባዩ አያይዘውም “በዓለም ምግብ ፕሮግራም ያሉ ባልደረቦቻችን እንደገለፁት በድርቅ በተጎዱት የሦስቱ ሀገራት የተለያዩ አካባቢዎች በዚህ ዓመት 5 ነጥብ 1 ሚሊዮን ህጻናት እጅግ ለበረታ የምግብ እጥረት እና የሰውነት መሟሸሽ ተጋልጠዋል።” ብለዋል።

‘የፊታችን መጋቢት ወር ይጥላል’ ተብሎ የሚጠበቀው ዝናብም ከአማካይ በታች እንደሚሆን ትንበያዎች አመላክተዋል። ዝናም ካልዘነበ እና ሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቱ በሚፈለገው መጠን ካልደረሰ የምግብ ዋስትና ዕጦቱ እየተባባሰ እንደሚሄድም ያለሙ የምግብ ፕሮግራም አስጠንቅቋል።

በድርቁ ሳቢያ የተከሰተውን አስከፊ ረሃብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለመቅረፍ ደብሊው ኤፍፒ የተቀናጀ የሁለትዮሽ አካሄድን በመከተል ላይ ነው ያሉት ዱጃሪች፣ “ከፍተኛ የአየር ንብረት መለዋወጥ የሚያስከትለውን ጉዳት የመቋቋም አቅምን በማጎልበት የህይወት

አድን አልሚ ምግቦች አቅርቦት በአፋጣኝ ማዳረስ መሆናቸውን አስረድተዋል።

XS
SM
MD
LG