በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ቃል አቀባይ ዕለታዊ ገለጻ


የተባበሩት መንግሥታት ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ
የተባበሩት መንግሥታት ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ

የዓለም ጤና ድርጅት በዱባይ ካለው የክምትች ጣቢያ 85 ሜትሪክ ቶን የሚሆን የህይወት አድን የመድሃኒት አቅርቦት ወደ ኢትዮጵያ መላኩን የተባበሩት መንግሥታት ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ ዛሬ በሰጡት እለታዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡

ቃል አቀባዩ “ይህ ከእሰዛሬዎቹ በድርጅታችን አባላት በአንድ ጊዜ በአየር ከተጓጓዙት ትልቁ የሰአብአዊ እርዳታ አቅርቦቶች አንደኛው ነው” ብለዋል ፡፡

መድሃኒቶች፣ የአሰቃቂ ሁኒታዎች ጊዜ መርጃዎች፣ አስቸኳይ ሁኔታ ቀዶ ጥገና መሳሪያዎች፣ የፍጆታ እቃዎች፣ የመገልገያ መሳሪያዎችና ኮሌራን ለመከላከል የሚረዱ እርዳታዎች እንደሚገኙበትም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

ለዚሁ አገልግሎት ብቻ የተመደበው አውሮፕላን፣ በተባበሩት ኤምሬት የተሰጠ መሆኑን ጠቅሰው ፣ እስከ 150 ሺ የሚደርሱ ሰዎችን አስቸኳይ ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል እርዳታ፣ ባላፈው ከጥቂት ቀናት በፊት አዲስ አበባ ማረፉን ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG