ዋሺንግተን ዲሲ —
ደቡብ ሱዳን ውስጥ ከቅርብ ቀናት ወዲህ ከ150 በላይ ሴቶች፤ የወሲብ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል ወይም ሌላ ከወሲብ ጋር የተያያዘ በደል ደርሶባቸዋል ይላል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት።
የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ ኃላፊ፣ ሄነሪታ ፎሪ፣ የድርጅቱ የሰብዓዊ ጉዳዮች ኃላፊ ማርክ ሎውኩክ እና የድርጅቱ የሕዝባዊ ፈንድ ሥራ አስኪያጅ ናታሊያ ካንመ ባወጡት የጋር መግለጫ መሰረት፣ የወሲብ ጥቃቱን የፈፀሙት ብዙዎቹ መለያ የለበሱ ታጣቂዎች ናቸው።
ሦስቱም ኃላፊዎች በጋራ በወሰዱት አቋም፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ሁሉ ድርጊቱን እንዲያወግዙና በአጥፊዎቹ ላይም ተገቢውን ዕርምጃ እንዲወስዱ አሳስበዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ