በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ለደቡብ ሱዳን ስደተኞች ያቀረበውን የዕርዳታ ጥያቄ ከፍ አደረገ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለደቡብ ሱዳን ስደተኞች ምግብ፣ ውኃና የጤና አገልግሎት ለማድረስ ያቀረበውን የዕርዳታ ጥያቄ ከ1 ቢልዮን ሁለት መቶ ሚሊየን ዶላር ወደ አንድ ቢልዮን 400 ሚሊየን ዶላር ከፍ አደረገ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለደቡብ ሱዳን ስደተኞች ምግብ፣ ውኃና የጤና አገልግሎት ለማድረስ ያቀረበውን የዕርዳታ ጥያቄ ከ1 ቢልዮን ሁለት መቶ ሚሊየን ዶላር ወደ አንድ ቢልዮን 400 ሚሊየን ዶላር ከፍ አደረገ፡፡

እጅግ የመረረ ግጭትና እየተባላሸ የመጣው የሰዉ ሕይወት ሁኔታ ደቡብ ሱዳናዊያንን ታይቶ በማይታወቅ ቁጥር ለመፈናቀልና ለስደት እየዳረገ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ አስታውቀዋል፡፡

በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ በመምጣቱ መጠን ከዓለም አቻ እንደሌለው በተነገረው መፈናቀልና ፍልሰት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ቁጥር ከ 1 ሚልዮን ስምንት መቶ ሺህ በላይ መሆኑንና ከመካከላቸውም አንድ ሚሊየን የሚሆኑት ሕፃናት መሆናቸውን ከፍተኛ ኮሚሽነሩ ተቋም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ደቡብ ሱዳናዊያኑ እየተሰደዱ ያሉት ወደ ሁሉም ጎረቤት ሃገሮች፤ ማለትም ወደ ዩጋንዳ፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኮንጎና ሴንትር አፍሪክ መሆኑን ኮሚሽነሩ አስታውቋል፡፡

በሃገር ውስጥም በርስ በርሱ ቁርቁስ ምክንያት 1 ነጥብ ስምንት ሚሊየን ደቡብ ሱዳናዊያን እየተፈናቀሉ ቀዬዎቻቸውን እየጣሉ መሸሻቸውን የኮሚሽነሩ መግለጫ ገልጿል፡፡

አሁን ያለውን የደቡብ ሱዳን ሁኔታ «ሊታሰብ የማይችል» እና «ገደል አፋፍ ላይ ያለ» ሲሉ የዓለም የምግብ መርኃግብር ኃላፊ ዴቪድ ቢስሌ ገልፀውታል፡፡

የዓለምአቀፍ ድጋፍ ጥያቄው እንደቀጠለ ቢሆንም ሃገሪቱ ውስጥ እርዳታ ለማድረስ እየተረባረቡ ያሉት የሕፃናቱ መርጃ - ዩኒሴፍ፣ የስደተኞች ጉዳዮች ተቋሙ ዩኤንኤችሲአር እና ምግብ አቅራቢው ዳብልዩ ኤፍ ፒ የሚፈለገው ገንዘብ በሚገባው መጠን አለመገኘቱን እያስታወቁ ናቸው፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG