ዋሺንግተን ዲሲ —
አንድ የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የጤና ድርጅት ባለሥልጣን በጦርነት ምክንያት ከሦስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለከባድ ረሃብ ስለተጋለጠባት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ደቡብ ምዕራባዊ ክፍለ ግዛት እያስጠነቀቁ ናቸው።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም የኮንጎ ተጠሪ ክሎድ ጂብዳር ሕዝቡ የሚፈልገው ሰላምን ነው ያን ደግሞ ከረድዔት ድርጅቶች አያገኘውም ብለዋል።
ባለፈው ዓመት ውስጥ ብቻ ከሦስት ሺህ በላይ ሕዝብ ካለቀበት አረመኔያዊ ሁከት ሸስቶ የተሰደደው የካሳይ ክፍለ ሀገር ሕዝብ አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን እንደሚሆን ባለሥልጣኑ አመልክተዋል።
የካሳይ ክፍለ ሀገር ሁኔታ እጅግ በጣም ከሚታወቁት የመንና ሦሪያ ከመሳሰሉት የቀውስ አካባባቢዎች የማይተናነስ ነው ብለዋል።
ሰፊዋ የማዕከላዊ አፍሪካ ሀገር ኮንጎ ባሁኑ ወቅት ከአፍሪካ በተፈናቃይ ሕዝብ ብዛት እንደኛ ነች።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ