በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ደቡብ ሱዳን በከፋ ሰብአዊ መብት ቀውስ ውስጥ ናት” ተመድ


የደቡብ ሱዳን ህፃናት በደቡብ ሱዳን በሚገኘው የስደተኞች ካምፕ አል ቃና
የደቡብ ሱዳን ህፃናት በደቡብ ሱዳን በሚገኘው የስደተኞች ካምፕ አል ቃና

በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የሰአብዊ መብት ኮሚሽን “አገሪቱ ለረጅም ጊዜ በከፍተኛ የሰብአዊ መብት ቀውስ እየተሰቃየች፣ ህዝቧም በድህነት፣ በአመጽና በደል ኡዙሪት ውስጥ ነው” ሲል አስጠንቅቋል፡፡ ይህን አስመልከቶ የተጠናቀረው ሪፖርትም ትናንት ሀሙስ ለመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንደሚለው በደቡብ ሱዳን ከሚገኙ 10 ክፍለ ግዛቶች፣ ዘጠኙ አስጊ በሆነ ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ተውጠዋል፡፡

ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን ከተቀዳጀች 10 ዓመታት በኋላ፣ እኤአ 2013 ላይ የተጀመረው የእርስ በርስ ግጭት እንዲቆም፣ በርካታ የሰላም ስምምነቶች ቢደረጉም ፣ወደ ከፍተኛ ደረጃ የደረሱትን ግጭቶች ሊያቆሙ አልቻሉም፡፡

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ያስሚን ሱካበተለይ በዋረን እና ሌክስ ስቴትስ በሚባሉት ግዛቶች ያሉት ግጭቶች ልዩ ትኩረት የሚሹ ናቸው ይላሉ፡፡

“በመጋቢትና ሀምሌ ወራት ውስጥ በዋረን እና ሌክስ ስቴትስ ውስጥ ህጻናትን ጨምሮ ከ56 ሰዎች በላይ ተረሽነዋል፡፡ እንዲህ ያሉት ህገወጥ ግድያዎች በገዢው ፓርቲ አባላል በሆኑ አስተዳዳሪዎች የሚፈጸም ሲሆን በሌሎችም ዘንድ በስፋት የተስፋፋ ሲሆን ብዙዎቹ በሰአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ናቸው፡፡”

ሪፖርቱ በግዴታ እንዲሰወሩ የተደረጉ፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከግጭት ጋርየተያያዙ ወሲባዊ ጥቃቶችና እንዲሁም ለውትድርና በግዴታ የሚመለመሉ ህጻናት በመላው አገሪቱ የሚታዩ ናቸው ብሏል፡፡

በስፋት የተሰራጨው ህገወጥትነትና ጥቃት የተባባሰ ሲሆን ለብዙዎች ሞትና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት ሆኗል፡፡

ከዚህ በተለየ መልኩ በኢኮኖሚው ዘርፍ ያለውን ወንጀል አስመልከቶ የወጣው የኮሚሽኑ ሪፖርት እንደሚያሳየው ደግሞ የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ባለሥልጣናት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ከህዝብ በመንጠቅ ወደግል አካውንቶቻቸው እያስገቡ መሆኑን አመልከቷል፡፡

የኮሚሽኑ አባል አንድሩ ክላፋም፣ ይህ የሰአብዊ መብትን የሚጥስ፣ የደህንነት ስጋት የሚፈጥር፣ 80 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ በከፋ ድህነት ውስጥ እንዲኖር የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG