አዲሱ የሶማልያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በትላንትናው ዕለት ሃገራቸው ወደ ቸነፈር ሊለወጥ የተረቃረበውን ረሃብ ለማስወገድ በያዘችው ጥረት ይረዳ ዘንድ ዓለምቀፉን ማኅበረሠብ ተማፅነዋል።
የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ማርግሬት በሽር እንደዘገበችው ስድሥት ሚሊዮን ሶማሌዎች የሠብዓዊ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ኮሌራ የሚያስከትለው በሽታም እያደገ መጥቷል።
አዲሱ የሶማልያ ፕሬዚዳንት ፋርማጆ ከዓለሙ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ጋር ከናይሮቢ የተነጋገሩት በቪድዮ መገናኛ አማካኝነት ነው፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ