የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተከራያት ሄሊኮፕተር በሶማሊያው አሸባሪው ቡድን አልሸባብ መያዟን የሚጠቁሙ ዘገባዎች አስመልክቶ ጥያቄ የቀረበላቸው የድርጅቱ ቃል አቀባይ ድርጊቱ መፈጸሙን አረጋግጠው “ለዚያ ምላሽ የሚሆኑ ጥረቶች እየተደረጉ ናቸው” ብለዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ትናንት ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ድርጊቱ በጋልጉዱድ ከተባለ ሥፍራ የተፈፀመ ሲሆን “በሄሊኮፕተሯ ተሳፍረው ለነበሩት ሰዎች ደህንነት ሲባል ላሁኑ ከዚህ ያለፈ የምንለው የለም” ብለዋል።
መድረክ / ፎረም