በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለም ዙሪያ ከ45ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለረሃብ መጋለጡ ተገለጸ


ፎቶ ፋይል፦የሁለት አመቱ አኮን ሞሮ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ለህመም የተጋለጠ ህፃን በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ በሚገኘው አል ሳባህ የህፃናት ሆስፒታል።
ፎቶ ፋይል፦የሁለት አመቱ አኮን ሞሮ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ለህመም የተጋለጠ ህፃን በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ በሚገኘው አል ሳባህ የህፃናት ሆስፒታል።

በዓለም ዙሪያ አጣዳፊ ረሃብ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ወቅት በአርባ ሦስት ሀገሮች የበረታ የረሃብ ቸነፈር አፋፍ ያለው ህዝብ ብዛት ወደአርባ አምስት ሚሊዮን ማሻቀቡን የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ፕሮግራም ገለጸ።

በዚሁ የአውሮፓ 2021 አርባ ሁለት ሚሊዮን የነበረው የጨመረበት ዋናው ምክንያት አፍጋኒስታን ውስጥ በተካሄደው የምግብ ዋስትና ግምገማ ሦስት ሚሊዮን የከበደ ረሃብ የተደቀነባቸው ሰዎች መጨመራቸው መሆኑን ነው ድርጅቱ የጠቆመው።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲቪድ ቢዝሊ "በብዙ አስር ሚሊዮኖች የተቆጠሩ ሰዎች መከራ ተደቅኖባቸዋል። ግጭቶች ኮቪድ-19 እና የአየር ንብረት ለውጥ ለአጣዳፊ ረሃብ የሚጋለጠውን ሰው ቁጥር እያገዘፉት ነው" ሲሉ ገልጸውታል።

በዓለም ዙሪያ የተደቀነውን የከበደ ረሃብ ለመቀልበስ የሚያስፈልገው ወጪ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ስድስት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ዶላር እንደነበር ያስታወሰው ድርጅቱ አሁን ወደ ሰባት ቢሊዮን እንዳደገ ነው ያስታውቀው። የአፍጋኒስታኑን እንዲሁም የመን እና ሶሪያ ውስጥ የቀጠሉትን ቀውሶች ጠቅሷል።

አጣዳፊ የምግብ ዕጦት ላይ ያሉ ቤተሰቦች የከበዱ አማራጮችን እንዲወስዱ እየተገደዱ ነው ያ ሴቶች ልጆቻቸውን ካለእድሜአቸው ይድራሉ፥ ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤት ያስወጣሉ ወይም አንበጣ እና የዱር ቅጠላ ቅጠል ያበሉዋቸዋል" ብሏል።

በኢትዮጵያ፣ በሶማሊያ፣ በአንጎላ፣ በኬንያ እና በቡሩንዲም አጣዳፊ ረሃብ ላይ ያሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑንም አክሎ ገልጿል።

XS
SM
MD
LG