በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን አቢዬ ሰላም ጥበቃ ጉዳይ በጸጥታ ምክር ቤት


ደቡብ ሱዳን ጎክ ማቻር ውስጥ ከተመደበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ጥበቃ ኃይል (ዩኒስፋ) ጋር በተያያዘ በጥልቅ ስላሽቆለቆለው ሁኔታ ለተ መ ድ የጸጥታ ምክር ቤት ገለጻ ተደርጎለታል።

ገለጻውን ያደረጉት በድርጅቱ የፖለቲካ እና የሰላም ግንባታ ክፍል የአፍሪካ ጉዳይ ምክትል ዋና ጸኃፊው መሆናቸውን የወጣው መግለጫ አመልክቱዋል።

እ አ አ መስከረም አስራ አራት ቀን የአንድ ኢትዮጵያዊ ሰላም አስከባሪ ህይወት የጠፋበትን ጨምሮ ጎክ ማቻር ውስጥ በቅርብ ጊዜያት በሰላም አስከባሪዎች ደህንነት ላይ የተደቀኑት አደጋዎች "በጥልቅ የሚያሰጉ ሆነው አግኝተናቸዋል" ሲሉ የጸጥታ ምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል።

የደቡብ ሱዳን መንግስት የሰላም አስከባሪውን ኃይል የተልዕኮ ስልጣኑን ያለ ዕንቅፋት እንዲያከናውን የማስቻል ሃላፊነቱን እንዲወጣ የሚሉ እና ሌሎችም ተያያዥ ጥያቄዎችን የምክር ቤቱ አባላት ማቅረባቸው ታውቋል።

XS
SM
MD
LG