በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶሪያዪቱ ዱማ ከተማ ውስጥ በተመድ ልዑካን ላይ ተኩስ ተከፍቶ ነበር


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በቅርቡ ኬሚካል ጥቃት ተፈፅሞባታል በተባለችው በሶሪያዪቱ ዱማ ከተማ ውስጥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑካን ላይ አነስተኛ ተኩስ ተከፍቶ እንደነበረ ተገለፀ።

በቅርቡ ኬሚካል ጥቃት ተፈፅሞባታል በተባለችው በሶሪያዪቱ ዱማ ከተማ ውስጥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑካን ላይ አነስተኛ ተኩስ ተከፍቶ እንደነበረ ተገለፀ።

የኬሚካል ጥቃቱን ምንነት ይፈትሻል የተባለው የመንግሥታቱ ድርጅት ቡድን ወደ ከተማዪቱ ሲዘልቅ የፈንጂ አደጋም ተደቅኖበት እንደነበረ ታውቋል።

የምርመራና ፍተሻ ቡድኑ አካባቢውን ለቅቆ እንዲወጣ ምክር ተሰጥቶት እንደነበር የዓለምቀፉ የኬሚካል የጦር መሣሪያዎች ክልከላ ድርጅት ዳይሬክተር አሕሜት ኢዙምሱ ተናግረዋል።

ሁኔታው የተፈጠረው ከትናንት በስተያ፣ ማክሰኞ ሲሆን ቡድኑ ወዲያው ተልዕኮውን አቋርጦ ወደ ዋና ከተማዪቱ ደማስቆ መመለሱን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

በአጋጣሚው በልዑካን ቡድኑ ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምንጭ ለቪኦኤ አረጋግጧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG