በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብጽ ኢትዮጵያና ሱዳን በጸጥታው ም/ቤት


የግብጽና የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአባይ ወንዝ ላይ በሚገነባው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ባላቸው አለመግባባት የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ጣልቃ እንዲገባ በትናንናትው ሀሙስ አቤቱታቸውን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

ባላፈው ሰኞ ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የሁለተኛ ምዕራፍ የውሃ ሙሌት መጀመሩዋን ይፋ ካደረገች በኋላ ውጥረቱ ተባብሷል፡፡ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜ ሿክሪ እንዲህ ብለዋል

“ይህ በግልጽ የታየው የአንድ ወገን የተናጥል ውሳኔ ኃላፊነት የጎደለውን የኢትዮጵያን አቋም ብቻ የሚያሳይ አይደለም፣ በዚህ ግድብ ሙሌት ግብጽና ሱዳን ላይ ሊደርስ ስለሚችለው ጉዳትም ደንታ ማጣት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ይህን ያደረገችው የሆኖ ሆኗል ተቀበሉት በሚል ግትርነት ውጤቱን አንድ አካል ላይ በግዴታ ለመጫን የምታደርገው መጥፎ አስተሳሰብ እንዲሁም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፈቃድ አለመገዛቷን የሚያሳይ ነው፡፡”

ወደ ሰሜን አቅጣጫ የሚፈሰው የአባይ ወንዝ አንደኛው ክፍሉ ነጭ አባይ ከቪክቶሪያ ሀይቅ ኡጋንዳ የሚነሳ ሲሆን ጥቁር አባይ ደግሞ የሚነሳው ከኢትዮጵያ ነው፡፡

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ሜርያም አልሳጂ አል መሀዲ የሚከተለውን ተናግረዋል

“ይሁን እንጂ የምክር ቤቱ ዝምታ የተሳሳተ መልዕክት የሚያስተላልፍ ሲሆን ይህ አደገኛ መዘዞች ያሉት፣ የሱዳንን ፍላጎትና ጥቅም የሚጎዳ ፣ በተናጥልና በአንድ ወገን የተወሰደው የሙሌት ውሳኔ፣ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ መሆኑን ያሳያል፡፡”

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ግድቡን መገንባት የጀመረችው እኤአ በ2011 ሲሆን ፣ እንደ ዋነኛው የውሃ ኃይል ማመንጫ ሆኖ የሚያገለግልና በመጠናቀቅ ላይ ያለ ፕሮጀክት ነው፡፡ የኢትዮጵያ የውሃ የመስኖና ኃይል ሚኒስትር ዶክተር ስለሺ በቀለ እንዲህ ይላሉ

“ውሃ በማጠራቀም ተርባይኖቹን በማንቀሳቀስ የኤሌክትሪ ኃይል እንዲያመነጩ ግድቦችን እየገነባን ነው፡፡ ለእናንተ መረጃ እንዲሆን ብንገራችሁ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከግብጹ የአስዋን ግድብ በሁለት ከግማሽ እጅ ያነሰ ነው፡፡ ምናልባት ታላቁ የህዳሴ ግድብን ከሌሎች ፕሮጀክቶች የተለየ የሚያደርገው 65 ሚሊዮን ለሚሆነውና ምንም ዓይነት የኤሌክትሪክ ኃይል የሌላቸው ኢትዮጵያውያንን የሚያነቃቃና ተስፋ የሚሰጥ መሆኑ ነው፡፡”

ከአስር ዓመታት ድርድር በኋላ ሶስቱም አገሮች አሁን ድረስ ለውዝግባቸው እልባት ሊሰጡት አልቻሉም፡፡ የምክር ቤቱም አባላት፣ ሶስቱም አገራት የጎላ ልዩነቶቻቸውን በቶሎ በመፍታት ተጨባጭ ወደ ሆነው ስምምነት እንዲደርሱ እያሳሰቧቸው ነው፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ!

ግብጽ ኢትዮጵያና ሱዳን በጸጥታው ም/ቤት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:00 0:00XS
SM
MD
LG