በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ የጸጥታ ምክር ቤት አዲሶቹን አባላት ተቀበለ


የስዊስ አምባሳደር ፓስካል ቤሪስዌል
የስዊስ አምባሳደር ፓስካል ቤሪስዌል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት አምስት አዳዲስ አባላትን ትናንት በይፋ ተቀብሏል።

ባለፈው ሰኔ ወር ያለምንም ተቃውሞ ለቀጣዩ የሁለት ዓመት ጊዜ ለምክር ቤቱ አባልነት የተመረጡት ኤኳዶር፣ ሞዛምቢክ፣ ጃፓን፣ ማልታ እና ስዊዘርላንድ ትናንት መቀመጫቸውን ይዘዋል።

የሞዛምቢክ አምባሳደር ፔድሮ አፎንሶ "ታሪካዊ ዕለት" ሲሉ የገለጹት ሲሆን የስዊስ አምባሳደር ፓስካል ቤሪስዌል በበኩላቸው ሁለቱ ሀገሮች ለመጀመሪያ ጊዜ የምክር ቤቱ አባል መሆናቸውን አስመልክተው "በጥልቅ ትህትና እና የኃላፊነት ስሜት" የማየው ነው ሲሉ ገልጸውታል።

አዲሶቹ አባላት እአአ በታህሳስ መጨረሻ የአባልነት ጊዜያቸው ያበቃውን ኬኒያ፣ አየርላንድ፣ ህንድ፣ ሜክሲኮ እና ኖርዌይን ተክተዋል።

XS
SM
MD
LG