በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኮሪያ የሚሳየል እና የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ሙከራ ላይ ተመድ

ሰሜን ኮሪያ እያካሄደች ባለው የሚሳይል ሙከራና የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ፕሮግራሟ ምክንያት ማዕቀብ እንዲጣልባት፣ የተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ ድምፅ የሚያሰጥ ውይይት እንደሚያካሂድ ተገለፀ።

ሰሜን ኮሪያ እያካሄደች ባለው የሚሳይል ሙከራና የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ፕሮግራሟ ምክንያት ማዕቀብ እንዲጣልባት፣ የተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ ድምፅ የሚያሰጥ ውይይት እንደሚያካሂድ ተገለፀ።

የአሁኑ ረቂቅ ውሳኔ የተዘጋጀው በዩናይትድ ስቴትስ ሲሆን፣ ፕዮንግያንግ ባለፈው ሳምንት ለ6ኛ ጊዜ ላካሄደችውና ሃይድሮጂን ቦምብ ነው ላለችው ሙከራ የተሰጠ መልስ መሆኑም ታውቋል።

የመጀመሪያው ረቂቅ ውሳኔ፣ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪን ጆን ያንግ እና መንግሥታቸው በውጪ አገር ያላቸውን ንብረት ጨምሮ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ማዕቀብ መጣል እንደሆነም ታውቋል።

ዛሬ ሰኞ ለፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ይቀርባል የተባለው ረቂቅ የማዕቀብ ውሳኔ፣ የፕሬዚደንት ኪም ጆንግና የመንግሥታቸውን ንብረት ማገድ አስቀርቶ፣ በነዳጅና በተፈጥሮ ጋዝ ላይ የሚጣለውን ማዕቀብ አሻሽሎ የሚያቀርብ እንደሆነም ተገልጧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG