በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብ አነሳ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

“ማዕቀቡ ከአሁን በኋላ አያስፈልግም” የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ። “ቀድሞውንም መሆን ያልነበረበት” የኤርትራ መንግሥት መግለጫ።

“ማዕቀቡ መነሳቱ ሳይሆን ቀድሞውንስ ለምን ተጣለ?” ይላል የኤርትራ መንግሥት

የምክር ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ። “ቀድሞውንም መሆን ያልነበረበት” ባለው ማዕቀብ መነሳት ሳቢያ ሃገሪቱ ላይ እስካሁን ለደረሰው ጉዳት ካሳ መከፈል አለበትም ብሏል።

በኤርትራ መንግሥትና ባለሥልጣናት ላይ የተነጣጠረው ማዕቀብ እንዲነሳ በብሪታንያ ተረቆ የቀረበውን ሃሳብ የጸጥታው ምክር ቤት በዛሬው ውሳኔው በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል።

አዲስ አበባ ላይ አስተያየት የሰጡት የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ በበኩላቸው “ማዕቀቡ ከአሁን በኋላ አያስፈልግም” ነው ያሉት።

ኤርትራ ለሶማሊያው እስላማዊ ጽንፈኛ ቡድን የመሳሪያ ድጋፍ ትሰጣለች በሚል የተባበሩት መንግሥታት ተቆጣጣሪዎች ያቀረቡትን ውንጀላ መሠረት በማድረግ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት አሥመራ ላይ ተጥሎ የቆየው ማዕቀብ የጦር መሳሪያ ግዥን ጨምሮ የኤርትራን መንግሥትና የወታደራዊ ባለሥልጣናት ጉዞ፣ እንዲሁም የማንኛውንም ዓይነት ንብረት እንቅስቃሴ የሚገድብ ነበር።

ኤርትራ ከጎረቤቷ ኢትዮጵያ ጋር የነበራት ፍጥጫ የተመላ ግንኙነት ወደ ሰላም መመለሱን እና ከጅቡቲም ጋር የነበራት ግንኙነት መሻሻሉ በመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት መግለጫ ይፋ ተደርጓል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብ አነሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:01 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG