በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ሰላም አስከባሪዎቹን ከኮንጎ ቀስ በቀስ ለማስወጣት ተስማማ


የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ በዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ
የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ በዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ

የተመድ የጸጥታ ምክር ቤት ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ሰላም አስከባሪዎቹን ከዚህ ከታሕሳስ ወር ጀምሮ ቀስ በቀስ ማስወጣት እንዲጀምር ያቀረበችውን ጥያቄ ለመቀበል ተስማማ፡፡

ሰላም አስከባሪዎቹ መውጣት ከነበረባቸው ከመጀመሪያው የጊዜ ሰሌዳ በአንድ ዓመት ቀደም ብሎ መሆኑ ነው፡፡

የጸጥታው ምክር ቤት በዚያች ሀገር ያለውን የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ስልጣን በአንድ ዓመት ያራዘመበት ውሳኔ ሰላም አስከባሪዎቹ ከደቡብ ኪቩ እስከመጪው ሚያዚያ መጨረሻ የሚወጡበትን ዕቅድ ያካተተ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ሰላም አስከባሪዎቹ ከአካባቢው የሚወጡት የተ መ ድ ስለምስራቅ ኮንጎ ሰላም ያለው ስጋት አሁንም እንደቀጠለ ባለበት ወቅት ነው፡፡ በግጭት የምትታመሰው ድሃዋ ሀገር ኮንጎ ረቡዕ እጅግ አሳሳቢውን ፕሬዚደንታዊ እና ምክር ቤታዊ ምርጫ ረቡዕ ታካሂዳለች፡፡ ምርጫው ታዲያ ሞኑስኮ በሚል ምህጻር የሚታወቀው የተመድ የሰላም አስከባሪ ኅይል የስልጣን ጊዜ ከሚያበቃበት ወቅት ጋር ተገጣጥሟል፡፡

በሀገሪቱ አሁንም ብጥብጥ ቢኖርም የኮንጎ መንግሥት የሰላም አስከባሪዎቹ መውጣት እንዲፋጠን ባለፉት በርካታ ወራት ሲወተውት ቆይቷል፡፡

የኮንጎ መንግሥት እንደሚለው የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራዊት ሲቪሉን ህዝብ ምስራቅ ኮንጎን ላለፉት ሠላሳ ዓመታት የወረሷት ታጣቂ ቡድኖች እና ሚሊሺያዎች ከሚያደርሱት ጥቃት ለመጠበቅ አልቻለም፡፡

ከኪንሻሳው ተመሳሳይ ወቀሳ የሰነዘሩ ሌሎችም የአፍሪካ ሀገሮች ያሉ ሲሆን ማሊ “ሚኑስማ” በሚል የምህጻር ስም የሚጠራው የዓለሙ ድርጅት ሰላም አስከባሪ ኅይል ባፋጣኝ እንዲወጣ ጠይቃለች፡፡

በቅርብ ጊዜያት ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ በርካታ የጸጥታ ምክር ቤት አባላት የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ኃይሎች ሰላም አስከባሪዎቹን ተክተው የህዝቡን ደህንነት ለማረጋገጥ መቻላቸው ላይ ጥርጣሬአቸውን አሰምተዋል፡፡

በተመድ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል አምባሳደር ሮበርት ዉድ “የኮንጎ መንግሥት ከሰላም አስከባሪዎቹ መውጣት በኋላ የሲቪሎች ጥበቃውን ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ ተረክቦ የሚያከናውነውን የጸጥታ ምክር ቤቱ በቅርበት ይከታተላል” ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG