በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ በሶሪያ እያየለ የመጣው በምድርና በአየር የታገዘ ወታደራዊ ዘመቻ እንዳሳሰበው ገለፀ


የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ

በደቡብ ምዕራብ ሶሪያ በቅርቡ እያየለ የመጣው በምድር እና በአየር ድብደባ የታገዘ ወታደራዊ ዘመቻ ክፉኛ ያሳሰባቸው መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ አስታወቁ።

በደቡብ ምዕራብ ሶሪያ በቅርቡ እያየለ የመጣው በምድር እና በአየር ድብደባ የታገዘ ወታደራዊ ዘመቻ ክፉኛ ያሳሰባቸው መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ አስታወቁ።

“በአዲሶቹ ጥቃቶች አብዛኞቹ ወደ ዮርዳኖስ ድንበር ያቀኑትን ጨምሮ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች ቀያቸውን ጠለው ለመሰደድ ተዳርገዋል። ሁኔታው ከሶሪያ ድንበር ተሻግሮ ለክልሉ ሰላምና መረጋጋትም አደጋ ደቃኝ ነው።” ሲሉ ዋና ፀኃፊ ጉቴሬሽ ሥጋታቸውን መግለፃቸውን የቃል አቀባያቸው ጽ/ቤት ይፋ ባደረገው የፁሁፍ መግለጫ አክሎ አመልክቷል።

“እያደር እያየለ የመጣው ወታደራዊ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲያቆም ሲሉ ጥሪ ያሰሙት የመንግሥታቱ ዋና ፀኃፊ “ሁሉም ወገኖች ያለባቸውን ኃላፊነት እና በዓለምቀፍ ሕጎች እና ሌሎች ዓለምቀፍ የሰብዓዊነት ድንጋጌዎች የታቀፉ ግዴታዎቻቸውን እንዲያከብሩ አሳስበዋል።

እአአ በሃምሌ 2017በደቡባዊ ሶሪያ የሚካሄደው ውጊያ እንዲያቆም የሚያስገድድ የተኩስ አቁም ሥምምነት በዩናይትድ ስቴትስ እና ሩሲያ መካከል እንዲደረስ ማደራደሯ ይታወሳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG