በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጉዳይ

ዋና ጸኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ
ዋና ጸኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ችግሮቻቸውን ፈትተው ግንኙነታቸውን ለማሻሻል አዎንታዊ ዕርምጃዎች መውሰዳቸውን ዋና ጸኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ በደስታ መቀበላቸውን አስታወቀ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ችግሮቻቸውን ፈትተው ግንኙነታቸውን ለማሻሻል አዎንታዊ ዕርምጃዎች መውሰዳቸውን ዋና ጸኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ በደስታ መቀበላቸውን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች በመካከላቸው መልካምና ዘላቂ ሰላም የተላበሰ ጉርብትና ግንኙነት ለመመስረት የያዙትን ጥረት ማድነቃቸውን ቃል አቀባያቸው ስቴፋን ዩጃሪክ በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል። የሁለቱ ሀገሮች ጥረት ለአጠቃላዩ የአፍሪካ ቀንድ አዎንታዊ እንድምታ እንደሚኖረው አክለው ገልፀዋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸኃፊ ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚያደርጉዋቸውን የንግግር ሂደቶች ለማጠናከር ሊጠቅሙ የሚችል ዕገዛ ሁሉ ለማድረግ ዝግጁነታቸውን ገልፀዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG