በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

23ሚሊዮን የሚደርሱ አፍጋኖች ለረሀብ መጋለጣቸውን ተመድ አስታወቀ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የተባበሩት መንግሥታት ሥር ያሉ ድርጅቶች በአፍጋኒስታን ያለው ሰብአዊ ቀውስ ታይቶ በማይወታወቅ መንገድ እያደገ ሲሆን በግጭት በተጎዳችው አገር 22.8 ሚሊዮን ህዝብ፣ በህዳር ወር ውስጥ “ከፍተኛ የምግብ እጥረት” እንደሚገጥመው አስታውቀዋል፡፡

የምግብና የግብርና ድርጅት እንዲሁም የዓለም ምግብ ፕሮግራም በጋራ ባወጡት ጥናት፣ ድርቅ፣ ግጭትና የኢኮኖሚው መውደቅ ተደማምረው፣ የሰዎችን ህይወት ክፉኛ እንደሚጎዱና የአፍጋን ዜጎችን የምግብ ተደራሽነት አደጋ ላይ እንደሚጥሉ አስረድተዋል፡፡

ከተጎጂዎም ውስጥ እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ወደ 3.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት በዓመቱ መጨረሻ ከፍተኛ በሆነ ያልተመጣጠነ የምግብ እጥረት እንደሚጎዱም ጥናቱ አመልክቷል፡፡

እየመጣ ያለው አደገኛው ክረምትም በምግብ እርዳታ የሚተማመኑ በርካታ የአፍጋኒስታን ቤተሰቦችንና አካባቢዎችን እንደሚጎዳም የተባበሩት መንግሥታት በጥናቱ ግኝት አስታውቋል፡፡

አፋጣኝ እርዳታ በቶሎ ካልተደረገ በርካታ የአፍጋን ዜጎች የሚኖራቸው ምርጫ አካባቢያውቸውን መልቀቅ ወይም እዚያው ቆይቶ መጭውን አደጋ መጋፈጥ እንደሆነ ተገልጿል፡፡፡፡

ታሊባን አፍጋኒስታንን ከተቆጣጠረ በኋላ የፋይናንስ ማዕቀብ በመታሰቡ ወደ 10 ቢሊዮን የሚሆን የአገሪቱ ገንዘብ በዩናትድ ስቴትስ እና በሌሎች ምዕራባውያን አገሮች እጅ ተይዞ እንደሚገኝም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG