በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምርጫ ዘገባ ወቅት ለጋዜጠኞች ደህንነት ጥበቃ እንዲደረግ ተመድ አስጠነቀቀ


በዩኔስኮ የንግግር ነፃነት እና የጋዜጠኞች ደህንነት ጉዳዮች ኃላፊ ጊለርሜ ካኔላ ደ ሱዛ ጎዶይ
በዩኔስኮ የንግግር ነፃነት እና የጋዜጠኞች ደህንነት ጉዳዮች ኃላፊ ጊለርሜ ካኔላ ደ ሱዛ ጎዶይ

አንድ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከፍተኛ ባለስልጣን ናቸው በምርጫ ወቅት በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱትን እነኝህን ጥቃቶች አስመልክቶ ድርጅትያቸው ያወጣውን ማስጠንቀቂያ ያሰሙት።

በዩኔስኮ የንግግር ነፃነት እና የጋዜጠኞች ደህንነት ጉዳዮች ኃላፊ ጊለርሜ ካኔላ ደ ሱዛ ጎዶይ በትላንትናው ዕለት በኒዮርክ ባቀረቡት አጭር ጋዜጣዊ መግለጫ፡ “በአለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕጎችም ሆነ የፀጥታው ምክር ቤት ከጉዳዩ ጋር አያይዞ ባሳለፋቸው ድንጋጌዎች በተመለከቱት መሰረት፡ ጋዜጠኞች በእነኚህ ሁኔታዎች ውስጥ ሥራቸውን መሥራት በሚያስችል መልኩ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል” ብለዋል።

የፀጥታው ምክር ቤት ድንጋጌ ቁጥር 2222’ን በተለይ የጠቀሱት የመንግስታቱ ድርጅት ባለስልጣን፡ የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደ ጠቆሙት፡ በተለያዩ አካባቢዎች በመካሄድ ላይ ያሉት ግጭቶች፡ ካሁን ቀደም ታይቶ በማያውቅ ደረጃ የበርካታ ጋዜጠኞችን ሕይወት እየቀጠፉ መሆናቸውን አስታውሰዋል።

ጎዶይ በትላንቱ የቪዲዮ መልዕክታቸው አያይዘውም፡ “እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2019 እስከ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ በ70 ሃገራት በተካሄዱ ምርጫዎች ወቅት፡ በጋዜጠኞች ላይ የተፈጸሙ

ጥቃቶችን የሚያሳይ ልዩ ጥናት አድርገናል” ብለዋል። በጥናቱም መሠረት በዝርዝር የተመዘገቡትን ጨምሮ 759 የመብት ጥሰቶች በጋዜጠኞች ላይ ተቃጥተዋል” ብለዋል።

“በመሆኑም ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁት፡ ቢያንስ በ81 አገሮች ውስጥ ምርጫ በሚካሄድበት 2024 የአሳሳቢነቱን ደረጃ ከፍ ማለት በመረዳት፡ ጋዜጠኞች የምርጫ ዘገባዎችን በሚያቀርቡበት ወቅት ደህንነታቸው መጠበቁን የሚያረጋግጡ እርምጃዎች የማዘጋጀትን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተን መግለጽ እንሻለን” ሲሉ አስረድተዋል።

በመካከለኛው ምስራቅ የሚካሄደው ግጭት በዚያ ለሚገኙ ጋዜጠኞች ደህንነት ደህንነት ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም፣ “ከአጋሮቻችን ጋር በመሆን ክትትላችንን እንቀጥላለን” ብለዋል። አክለውም፡ በዲጂታል መረጃው ዓለም የሚታዩትን ትንኮሳዎች፣ የደህንነት ጥያቄዎች፣ የተሳሳቱ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮችን በተመለከተም አዲስ የአፈጻጸም መመሪያ ይፋ መደረጉን ገልጠዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG