በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቬነዝዌላ ጉዳይ ተመድ ጥሪ አቀረበ


የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሚሼል ባሽሌ
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሚሼል ባሽሌ

በቬነዝዌላ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ ወጥተው ብዙ ደም ከመፋሰሱ በፊት ሰላማዊ ንግግር እንዲጀመር የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሚሼል ባሽሌ ጥሪ አቀረቡ።

በቬነዝዌላ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ ወጥተው ብዙ ደም ከመፋሰሱ በፊት ሰላማዊ ንግግር እንዲጀመር የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሚሼል ባሽሌ ጥሪ አቀረቡ።

ባሽሌ በተጨማሪም - የቬነዝዌላ ፀጥታ ኃይሎች በዚህ ሣምንት የተቃውሞ ሰልፍ ወቅት 20 ሰዎችን መግደላቸውን ከ350 በላይ ይዘው ማሠራቸው በነፃ አካል እንዲመረመር ጠይቀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በደቡብ አሜሪካዊቷ ሃገር ወደ ዲሞክራሲ ሰላማዊ ሽግግር ካልተደረገ አማራጮች ሁሉ ክፍት ናቸው ሲሉ ትላንት ኒኮላስ ማዱሮን በግልፅ አስጠንቅቀዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ይፋ ዕውቅና የምትሰጠው ለብሄራዊ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ለሁዋን ጉዌዶ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ትረምፕ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ መናገራቸውን ተከትሎ አወዛጋቢው የቬነዝዌላ ፕሬዚዳንት ማዱሮ ሃገራቸው ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደምታቋርጥ አስታውቀዋል።

ማዱሮ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ቬነዝዌላን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ የሰጡት 72 ሰዓት ብቻ ነው።

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖፔኦ ግን ማዱሮ ከእንግዲህ በኋላ ሥልጣን ስለሌላቸው እንዲህ ዓይነቱን ትዕዛዝ ማስተላለፍ አይችሉም ብለዋል።

ከ34ቱ የደቡብ አሜሪካ ሃገሮች ድርጅት /OAS / 16ቱ ትላንት የቬነዝዌላ የሽግግር ፕሬዚዳንት ሲሉ ድጋፍ የሰጡት - ለተቃዋሚው የብሄራዊ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ለሁዋን ጉዌዶ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG