በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ትግራይ ውስጥ ስላለው የሰብዓዊ ሁኔታ እና የኤርትራውያን ስደተኞች ጉዳይ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት የስደት ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፕ ግራንዲ
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት የስደት ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፕ ግራንዲ

ትግራይ ውስጥ ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ በእጅጉ እንደሚያሳስባቸውና እዚያ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ጉዳይም አደጋ ላይ ናቸው ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የስደት ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፕ ግራንዲ ትናንት አስታውቀዋል።

ክፍተኛ ኮሚሽነር ግራንዲ ትናትን ባወጡት መግለጫ ምንም እንኳን ምግብ በተወሰኑ የስደተኞች መጠለያዎች ውስጥ እየተከፋፈለ ቢሆንም ቢያንስ በሌሎች ሁለት ሠፈሮችን ጦርነቱ ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ መድረስ አልመቻሉን አመልክተዋል።

“በእነዚያ ሠፈሮች ውስጥ ያለ ኤርትራውያን ስደተኞች ዕጣ አብዝቶ አሳስቦኛል” ብለዋል ግራንዲ።

ግጭቱ ከመቀስቀሱ በፊት በአራት ሠፈሮች ውስጥ 96 ሺህ ኤርትራውያን ሰደተኞት ተጠልለው እንደነበር ዩኤንኤችሲአር አስታውቋል።

የኮሚሽነር ግራንዲ የፅሁፍ መግለጫ እንደሚለው ኤርትራውያኑ ስደተኞች ለብዙ ሣምንታት እርዳታ ሳይደርሳቸው ቆይቷል። በተጨማሪም ከታመኑ ምንጮችና ችግሩን በቀጥታ ካስተዋሉ ያገኘሁት ሲል ከፍተኛ ኮሚሽነሩ ባሰፈሩት መልዕክት ግድያን፣ ያነጣጠረ ጠለፋና በኃይል ወደ ኤርትራ መመሰስን ጨምሮ አየተፈፀሙ ናቸው ያሏቸው የደህንነት አለመኖርና ብርቱ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች አበርትተው ከሚያስጨንቋቸው ጉዳዮች መካከል መሆናቸውን ገልጸዋል።

ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ብዙዎች ስደተኞች ወደ ሱዳንና አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መሸሻቸውንም ግራንዲ ጠቁመዋል።

XS
SM
MD
LG